Post #304
441 አብራክ ዛሬ ከሆስፒታል ይወጣል ።
22/11/2018ዓ.ም
Post #303
973
Forwarded from Silas Godana
ማስታወቂያ
በ2019 ትምህርት ዘመን ትምህርታችሁን በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ሞዴል ት/ቤት ለመማር የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፣
1. ምዝገባ የሚካሔደዉ ከ21/11/2018 ዓ.ም. እስከ 05/12/2018 ዓ.ም. ይሆናል፡፡
2. በዋናዉ ግቢ ቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 12ኛ እንዲሁም አባያ ግቢ ቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 6ኛ ክፍል ለመማር ለምፈልጉ ሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደዉ በአንድ ማዕከል በዋናዉ ግቢ መደበኛዉ ት/ቤት ይሆናል፡፡
ለምዝገባ በምትመጡበት ጊዜ ማሟላት ያለባችሁ፡-
Ø ለነባር ተማሪዎች
1. የድጅታላይዘሽን 200 ብር እና የምዝገባ 300 ብር በድምሩ ብር 500.00 በአካዉንት ቁጥር 1000726844163 በማስገባት ባንክ ያስገቡበትን ስሊፕ ይዞ መቅረብ፡፡
2. በ2018 ወደሚቀጥለዉ ክፍል ያለፉበት ካርድ ማቅረብ፡፡
3. የፋይዳ መታወቂያ ካርድ
Ø ለአዲስ ተማሪዎች
1. በ2018 ዓ.ም. የተማሩበትንና ወደሚቀጥለዉ ክፍል ያለፉበት ካርድ ማቅረብ፤
2. ጸባይ መግለጫ ማስረጃ ማቅረብ፤
3. የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ የሚወሰነዉ የሚሰጠዉን የመግቢያ ፈተና ካለፉ ሲሆን ክፊያ የምትፈጽሙና የሚመዘገቡት ከዚያ በኋላ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፤
የትምህርት ቤታችንን ድጅታላይዘሽን ስራ የሚያካሒደዉ ኩባኒያ ፍላጎቱ ያላቸዉን ተማሪዎች መሠረት በማድረግ በፋብሪካ ዋጋ ደብተር ስክርቢቶ፤ቦርሳና ዩኒፎርም ለማቅረብ ስለሚፈልግ ፍላጎት የማሳወቂያ ምዝገባ ስለምናካሒድ ዕድሉ እንዳያመልጣችሁ እናሳስባለን፡፡
Post #302
373 በድጋሚ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አብራክ ከፅኑ ህሙማን ክፍል ወጥቶ ማናገር ጀምሯል ። በወላጆቹ ስልክ ማግኘት ትችላላችሁ ። 19/11/2018ዓ.ም 11:30
Post #301
432 እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን ቀዶ ጥገናው በሠላም ተጠናቋል ።
ለእናት እና አባት እዬደወላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በሉ።
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ።
17/11/2018ዓ.ም ከቀኑ 6:20
Post #300
431 ውድ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፣የተማሪ ወላጆች አብራክን እና ወለጆችን ለማግኘት ከፈለጋችሁ
+251912790166 (እናት) አካሌ
+251924442311(አባት ) ንዋይ
Post #298
431 "አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ አትደንግጥ፤ እኔ አምላክህ ነኝና፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሃለሁም።" — ኢሳይያስ 41፥10
"ለእግዚአብሔር የማይቻለው ነገር የለም።" — ሉቃስ 1፥37
ፈጣሪ ይጠብቅህ፣ ቀዶ ጥገናህን በሰላም ያሳልፍህ፣ ፈጥነህም ሙሉ ጤንነትህን ይመልስልህ። ሁላችንም በጸሎትና በፍቅር ከጎንህ ነን።
"ውድ ልጅ አብራክ ፣ አንተ ብርቱ ነህ። ዶክተሮችና ነርሶች በጥንቃቄ ይንከባከቡሃል፣ ይህም በፍጥነት እንድትድንና ወደ ትምህርትህ፣ ወደ ጓደኞችህ እና ወደምትወዳቸው ጨዋታዎች እንድትመለስ የሚረዳህ ነው። አንተ ብቻህን አይደለህም፤ ቤተሰብህ፣ ጓደኞችህ እና መምህራንህ ሁሉ ከጎንህ ናቸው። በአምላክ ተስፋ አድርግ፤ ሁሉም መልካም ይሆናል። ፈጥነህ እንድትድን እንመኛለን።"
Post #297
401 ተማሪ አብራክ ንዋይ የልብ ቀዶ ህክምና ሐሙስ ማለትም በቀን 16/11/2018 ምሽት 6:00 ስለሆነ ሁላችሁም በፀሎት ከጎኑ እንድትሆኑ ።
Post #296
452 1. Abenezer Asegid Bula
2. Abenezer Tamirat Abebe
3. Abeselom Habitamu Molla
4. Abrak Niway Demisse
5. Adonis Akililu Alemayehu
6. Amesias Bogale G/Mariam
7. Amir Seid Mohammed
8. Banchwesen Tedila Kebede
9. Betselot Demelash Kumsa
10. Betselot Asfaw Tesfaye
11. Dibora Wanzahun Godana
12. Edilawit Mikire Danka
13. Eleni Mekonin Tadese
14. Elishaday Mezigebu Getahun
15. Eyuel Atinafu Abriham
16. Fikireselam Tadese Mamido
17. Firehiwot Teferi Htuye
18. Kalkidan Hakime Ayele
19. Lewi Tefera Ashebo
20. Liul Habtamu Wase
21. Loza Birhanu Gemeda
22. Mahlet Mamush Woiza
23. Mekilit Mintesnot Tobe
24. Melat Beyene Tora
25. Meron Alemayehu
26. Merry Mohammed Kunta
27. Mintesinot Daniel Geresu
28. NatanWanzahunGodana
29. Rekik Tesfaye Tadesse
30. Saron Elias Markos
31. Sewunet Addisu Tonja
32. Sinishat Dubusha Aweke
33. Sofia Tarekegn Tadesse
34. Surafel Mamushet Zewude
35. Yeabsira Birako Betso
36. YeabtsegaKassayeCheneke
37. Yididiya Alemayehu Petros
38. Yordanos Mengistu Haile
Post #295
410 Maths
English
General Science
Social study
የ 7ኛ እና የ8ኛ ክፍልን እያነበባችሁ ቆዩ።
እንዳትዘነጉ ። መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል ።
Post #293
471 አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጵያውያን!
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ለመጀመር ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ እና አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ የፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት፣ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ ከሚገቡት መካከል አንዱ የሆነው የአርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር-ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የትምህርት ቤቱ ቋሚ ሕንጻ ግንባታ ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ፣ በ2019 የትምህርት ዘመን ጊዜያዊ የመማር-ማስተማር ሥራውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኩልፎ ካምፓስ ውስጥ የሚያካሂድ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን።
ይህ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ፣ በላቀ የትምህርት አፈጻጸማቸውና በውጤታቸው እጅግ የላቁና ምርጥ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር በመሆኑ ለአገራዊ አንድነትና ለልዩ የክህሎት ልማት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ መሳካትና ለሂደቱ ውጤታማነት አስፈላጊውን ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
ከተማሪዎች ምዝገባና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ዝርዝር መመሪያዎች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ
መልካም የትምህርት ዘመን!
Post #291
457 ውድ ልጆቼ (ተማሪቼ) በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ። አመቱን በፈጣሪ እርዳታ በስኬት ጨርሰናል። በያላችሁበት እንዴዬ ኃይማኖታችሁ ፈጣሪን ከልባችሁ አመስግኑ። እኔ ዛሬ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።
27/10/2018ዓ.ም
Post #290
484 ውድ ተማሪዎች እስከአሁን የተለቀቀው
የሚኒስትሪ ውጤት የሀረሪ ክልል እና የአዲስአበባ የ 8ኛ ክፍል ሲሆን
ውጤት ሲለቀቅ
ቀድመን የምናሳውቃችሁ ይሆናል
Post #289
510 የሚንስትሪ ውጤት እስክለቀቅ ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ
Post #287
642 የተማሪ አብራክ ነዋይ ለልብ ህክምና የተደረገ ድጋፍን በተመለከተ
ለተማሪ አብራክ ነዋይ ለልብ ህክምና በተማሪዎች ፣ በመምህራን እና በትምህርት ቤት አስተዳደር አካላት አማካኝነት የተሰበሰበ ገንዘብ 234,487(ሁለት መቶ ሠላሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሰባት ብር) ነው። ይህ ገንዘብ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ሌሎች አካላት በባንክ ያስተላለፉትን ሳያጠቃልል በተማሪዎች እና በመምህራን አማካኝነት ተሰብስቦ በመምህር አንደነት ጀርሣ አማካኝነት ወደ ወላጆቹ የጋራ አካውንት ገቢ የተደረገ ብር ሲሆን።
ምስጋና ከፈጣሪ በመቀጠል ይህ በጎ አላማ እንድሳካ ለተባበሩት አካላት ሁሉ ይሁን ።
ልዩ ምስጋና
1. ለአርባምንጭ ከተማ ትምርህት መምሪያ፣
2. ሻራ ሙጃ፣ ሻራ ቤተሔል፣ ሻራ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ፣ ሻራ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ፣ ሻራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ደብር አስተዳዳሪ ፣ ልማት ሙሉ አንደኛ ደረጃ ፣ ልማት ሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ፣ ልዩነህ ድባሌ አካዳሚ ፣ ሆልሰቨር አካዳሚ ፣ ርሆቦት ፣ ጋሽ አሰፋ ጨቦ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ፣ አባያ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ፣ ሐረግ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ የትነበርሽ አንደኛ ደረጃ፣ ጫሞ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ፣ ማህቶት አካዳሚ ፣ ህብረት ለልማት ፣አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ ቤቶች ር/መምህራን ፣አስተዳደር አካላት ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች
3. ለአርባምንጭ ከተማ ማህበረሰብ በሙሉ
4. ለጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አድማሱ እና ካቢንያቸው
5. ለአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ እና ካቢንያቸው
6. ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለአቶ ወደፊት ኃይለማርያም
7. ለትምህርት ቤታችን ለ8ኛ እና ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች
8. ድጋፉን ላስተባበሩ ለትምህርት ቤታችን መምህራን ፦
መ/ር ኡንዴና ኡርቃ፣
መ/ርት መብራት አየለ ፣
መ/ርት ታደለች አይሣ ፣
መ/ር እንድሪያስ እጅጉ ፣
መ/ር ዮሐንስ ጫንጨ ፣
መ/ር ኦድሮ አሻ ፣
መ/ር ተናገር ይስማቸው እና
መ/ር አንድነት ጀርሣ
በመጨረሻም፡- የልብ ቀዶ ጥገናው የሚከናወነው ሐምሌ 8/2018ዓ.ም ሲለሆነ ሁላችንም በፀሎታችን ከጎኑ እንድንሆን ይሁን፡፡
Post #286
490 እግዚአብሔር ይክበር ፤ይመስገን በሠላም አጠናቀናል ።12/10/2018ዓ.ም
Post #285
541 የሒሳብ መምህራችሁ 10/10/2018ዓ.ም
Post #284
555 7 አመቱን ሙሉ ለነበረን ቤተሰባዊ
አገልግሎት Thank you
እኔ ሁሌም እወዳችኋለሁ መልካም
ነገርን ሁሉ እመኝላችኋለሁ❤