አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጵያውያን!
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ለመጀመር ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ እና አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ የፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት፣ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ ከሚገቡት መካከል አንዱ የሆነው የአርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር-ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የትምህርት ቤቱ ቋሚ ሕንጻ ግንባታ ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ፣ በ2019 የትምህርት ዘመን ጊዜያዊ የመማር-ማስተማር ሥራውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኩልፎ ካምፓስ ውስጥ የሚያካሂድ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን።
ይህ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ፣ በላቀ የትምህርት አፈጻጸማቸውና በውጤታቸው እጅግ የላቁና ምርጥ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር በመሆኑ ለአገራዊ አንድነትና ለልዩ የክህሎት ልማት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ መሳካትና ለሂደቱ ውጤታማነት አስፈላጊውን ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
ከተማሪዎች ምዝገባና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ዝርዝር መመሪያዎች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ
መልካም የትምህርት ዘመን!
Post #293
471
- 👍 3