ማስታወቂያ
በ2019 ትምህርት ዘመን ትምህርታችሁን በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ሞዴል ት/ቤት ለመማር የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፣
1. ምዝገባ የሚካሔደዉ ከ21/11/2018 ዓ.ም. እስከ 05/12/2018 ዓ.ም. ይሆናል፡፡
2. በዋናዉ ግቢ ቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 12ኛ እንዲሁም አባያ ግቢ ቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 6ኛ ክፍል ለመማር ለምፈልጉ ሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደዉ በአንድ ማዕከል በዋናዉ ግቢ መደበኛዉ ት/ቤት ይሆናል፡፡
ለምዝገባ በምትመጡበት ጊዜ ማሟላት ያለባችሁ፡-
Ø ለነባር ተማሪዎች
1. የድጅታላይዘሽን 200 ብር እና የምዝገባ 300 ብር በድምሩ ብር 500.00 በአካዉንት ቁጥር 1000726844163 በማስገባት ባንክ ያስገቡበትን ስሊፕ ይዞ መቅረብ፡፡
2. በ2018 ወደሚቀጥለዉ ክፍል ያለፉበት ካርድ ማቅረብ፡፡
3. የፋይዳ መታወቂያ ካርድ
Ø ለአዲስ ተማሪዎች
1. በ2018 ዓ.ም. የተማሩበትንና ወደሚቀጥለዉ ክፍል ያለፉበት ካርድ ማቅረብ፤
2. ጸባይ መግለጫ ማስረጃ ማቅረብ፤
3. የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ የሚወሰነዉ የሚሰጠዉን የመግቢያ ፈተና ካለፉ ሲሆን ክፊያ የምትፈጽሙና የሚመዘገቡት ከዚያ በኋላ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፤
የትምህርት ቤታችንን ድጅታላይዘሽን ስራ የሚያካሒደዉ ኩባኒያ ፍላጎቱ ያላቸዉን ተማሪዎች መሠረት በማድረግ በፋብሪካ ዋጋ ደብተር ስክርቢቶ፤ቦርሳና ዩኒፎርም ለማቅረብ ስለሚፈልግ ፍላጎት የማሳወቂያ ምዝገባ ስለምናካሒድ ዕድሉ እንዳያመልጣችሁ እናሳስባለን፡፡
Post #303
973
Forwarded from Silas Godana
- ❤ 5
- 👍 3