"አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ አትደንግጥ፤ እኔ አምላክህ ነኝና፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሃለሁም።" — ኢሳይያስ 41፥10
"ለእግዚአብሔር የማይቻለው ነገር የለም።" — ሉቃስ 1፥37
ፈጣሪ ይጠብቅህ፣ ቀዶ ጥገናህን በሰላም ያሳልፍህ፣ ፈጥነህም ሙሉ ጤንነትህን ይመልስልህ። ሁላችንም በጸሎትና በፍቅር ከጎንህ ነን።
"ውድ ልጅ አብራክ ፣ አንተ ብርቱ ነህ። ዶክተሮችና ነርሶች በጥንቃቄ ይንከባከቡሃል፣ ይህም በፍጥነት እንድትድንና ወደ ትምህርትህ፣ ወደ ጓደኞችህ እና ወደምትወዳቸው ጨዋታዎች እንድትመለስ የሚረዳህ ነው። አንተ ብቻህን አይደለህም፤ ቤተሰብህ፣ ጓደኞችህ እና መምህራንህ ሁሉ ከጎንህ ናቸው። በአምላክ ተስፋ አድርግ፤ ሁሉም መልካም ይሆናል። ፈጥነህ እንድትድን እንመኛለን።"
Post #298
431
- ❤ 6