በዚህ ፅሁፍ ከብዙ ሰዎች ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቻለሁ::
ሰዎች አንተ ላይ ለሚያደርጉት ካንተ ተቃራኒ አንተን የሚያናድ ነገሮችን ያንን ለምን አደረጋቹ ብለህ አትጠይቃቸው ምክንያቱም ያን ያደረጉበት ላንተ የሚያቀርቡትን ቆንጅዬ ምክንያት አዘጋጅተው ነውና የሚጠብቁህ ያውም አንተ ልክ እንዳልሆንክ የሚያረጋግጥ ምክንያት::
ሚስኪኑ አንተ ግን.....ስለነገሩ ግራ ተጋብተህ የማታውቀው ምክንያት ተደርድሮልህ ልክ በሆንከው ነገር ጥፋተኛ ተብለህ ይፈረድብሃል ይቅርታ ጠያቂውም አንተ ትሆናለህ.............
ይሁን ዛሬን እውነትን ይዘህ መሸነፍህ የሆነ ጊዜ ላይ አንተ ልክ እንደነበርክ ያረጋግጥልሃል::
በህይወቴ ውስጥ አንድ የተረዳሁት ነገር በየትኛውም የህይወት አጋጣሚ ሁሌም ሰዎች ባንተ ላይ እሸናፊዎች ሆነው መታየት ይፈልጋሉ በብዙ ነገር የነሱን የበላይነት ለማሳየት ይፈልጋሉ ቀድመህ የጀመርከውን ነገር እየሰራህ እየሞከርክ ይመጡና ቲቲቲ እንደዚ አይደለም አምጣው እኔ ልሞክረው ይላሉ ድንገት ሲሳካላቸው የበላይነታቸውን ያውጁብሃል አየኽ አ.....ምናምን እያሉ ብዙ የጉራ ቃላቶችን ይደረድራሉ....አለቃህ ፊት ብዙ የዙ የውሸት ቃላትን እየደረደሩ እነሱ ከነገሩ አምልጠው ሁሉንም ጥፋት የችግሩን ኃላፊነት ወዳንተ ያዞሩታል በሃሳብም የነሱን ሀሳብ እንዲደመጥ ይፈልጋሉ::
#ልክነታቸው_በያዙት_ሀሳብ_ልክ_መሆኑ_ላይ_ሳይሆን_አንተን_ተሸናፊ_ማድረግ_ላይ_ነው::
#ደስታቸው_በአንተ_ላይ_የበላይነታቸውን_ማወጅ_ላይ_ነው::
ከዙሪያቸውም የበላይነታቸውን የሚያውጁላቸው ቲፎዞን በአይናቸው ይፈልጋሉ ይሳካላቸዋልም በሳቅ እና በጭብጨባ የሚያጅቧቸው ተመሳሳይ እነሱ አሏቸው.............
ይሔ ሀሳቤን ስገልፅላቸው ልክ አይደለም ብለውም ሌላ የክርክር ርዕስን ይከፍታሉ........አሁንም እንደገና..............በድጋሚ
ስለዚህ ይህ ነገር ሲገባኝ በህይወቴ እንደዚ ማድረግ ጀመርኩ በቃ ለሰዎች ተሸናፊ ሆኜ መቅረብ ጀመርኩ አው አሺ ልክ ነህ አዎ ልክ ነሽ አዎ እሺ ልክ ናችሁ እላለሁ የሰውኛ ባህሪያቸውን ተረድቼ ማሸንፍ ብቻ እንደሚፈልጉ ስለማውቅ እኔ ጋር ሲመጡ ሁሌም አሸናፊ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ.......ይደሰቱ እሸነፍላቸዋለሁ እኔ ልክ መሆኔ እኔ እና እግዚአብሔር ማወቃችን ብቻ ይበቃል ለነገሩ የነሱ ልቦናውም ያውቀዋል ምክንያቱም የሰው ልጅ ሌሎችን በማስመሰል ውሸቱን እውነት እድርጎ ያቀርባል ያሳምናል እራሱን ግን መዋሸት አይችልም ለዛም ነው ውሸታሞች ሰላም የሌላቸው ሌሎች ሳይሆን እራሳቸው እራሳቸውን ስለሚወቅሱ::
የኔ ልክ መሆን አንተን እና ሌሎችን እስካልጎዳ ድረስ እኔን ተወኝ ልክ አይደለህም አትበልኝ:: ወጥረኽ ይዘህ ከሞገትከኝ ግን እሺ ልክ ነህ ብዬህ ይቅርታ ጠይቄህ አመልጥሃለሁ:: ነገ ባይሆንም ምናልባት የሆነ ቀን ትረዱኝ ይሆናል ደሞም አብዛኞቹ ጟደኞቼ የዛኔ ልክ መሆኔ የሚገባቸው ቆይቶ ነው በነሱ አገላለፅ ደግሞ ትላንትን ተሸንፈህ ዛሬን ማሸነፍ ደግሞ ደስ ሚል ነገር ነው..ህህ........
እኔ ግን ልክ አለመሆናቸውን ተረድተው ትላንት የደገሙትን ስህተት ዛሬ.....ነገ እንዳይደግሙት ነው ፍላጎቴ ምክንያቱም ትላንት ላይ በኛ ልክ ነን ባይነት ያጣናቸውን ሰዎችን ያሳጣናቸው ነገሮች ብዙ ናቸውና ቆም ብለን ማሰብ አለብን::
ዛሬን ተሸንፎ...........ነገ ደግሞ ትላንት ተሳስተው ያሸነፋንን የመሰላቸውን ሌሎችን ከስህተታቸው ተመልሰው ለነገ ህይወታቸው አሸናፊ ማድረግ ደስ የሚል ነገር ነው::
ህይወት እንደዚህ..............ህይወት እንደዛ.........
የህይወቴ አንዱ ምልከታ........
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ (
@jahABP )
አስተያየታችሁን አድርሱኝ