እራሴን ካወኩት ጀምሮ ሰዎች በብዙ ነገሮች በጣም አድርገው ኮርኩመውኛል ህመምን አውቀዋለሁ መገፋትን አውቀዋለሁ ዝቅ መደረግን አውቀዋለሁ በህይወቴ በጣም የሚያስፈልገኝ ነገር ተነጥቄያለሁ አጥቻለሁ እሱን ህመም አውቀዋለሁ ቤተሰብህ ሲገፉ ሚሰማውን ስሜት እሳት ከመጨበጥ በላይ የሆነውን ህመም አሳልፌያለሁ እናቴን አባቴን ሰዎች ሲያሸማቁብኝ ሲኮሮኩሙብኝ እነሱን ለመጣል ሰዎች ደፉ ቀና ሲሉ አውቃለሁ:: እኛን ለማሳደግ ብዙ ስድቦችን እና መከራዎች እንደታገሱ አይቼ አድጌያለሁ እኔንስ እንዴት ባለ ትግስት ነው ያሳደጋችሁኝ::
እናቴና አባቴ በጥላቻ አላሳደጉኝም በፈሪሃ እግዚአብሔር እንጂ ይቅር ማለትን ከራስ ይልቅ ለሰዎች መኖርን እንጂ ለብዙሃን ደስታ መሆንን እንጂ::
ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግን እንጂ መፀለይን ወደእግዚአብሔር ማንጋጠጥን እንጂ ክፉን በክፉ ብለው አላስተማሩኝም:: እግዚአብሔር ስለሰጡኝ መልካሙን ስላሳዩኝ ሁሌም አመሰግናቸዋለሁ::
አሁን ላይ ለኔ አዲስ ነገሬ ፍቅር ደስታ እንጂ ሐዘንና ጉዳት ብዙ ጊዜ አብረን ስለኖርን አሁን ላይ ለኔ ምንም ናቸው::
ለኔ ከጉዳት ይልቅ መልካም ነገር ፍቅርን እነሱ ጋር ጥሩ ቦታ የሚሰጡኝ ሰዎች ናቸው አዲሶቼ ::
ውሸታሞች አስመሳዮችና ክፉዎች እኔ ጋር ብዙ አመት የስራ ልምድ አላቸውና የመቀጠር እድል የላቸውም ማመልከቻቸው በአንድ ቀን ቆይታ ይቀደድባቸዋል ከልምድም እንዲሁ ሲታዩ የሚያስታውቁም አሉ::
@jahABP ነኝ ይቀጥላል
Post #2239
520