TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2792 1.5K
#የሞት_ሞት

           "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን
               እጠይቀው ነበር በተገናኝን
           ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?"

ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካዔል ይህችን ጥልቅ ስንኞች ያሏት አጭር ግጥም ፅፈው ነበር:: ጋሽ ከበደ ምናልባት  በዚያኛው ዓለም ጠቢቡ ሰለሞንን የማግኘት ዕድል ገጥሟቸው ይጠይቁት ይሆናል:: ሆኖም እርሳቸው "ሞት የሚሞትበት ጊዜው መቼ ነው?" ብለው ወደኃላ ዘመን ተጉዙው የብሉይ ኪዳኑን ሰው ጠየቁት እንጂ ሞት እንኳን ከሞተ ድፍን ሁለት  ሺህ ዓመታት አልፈውታል::

ለዘመናት ባለስልጣን ሆኖ ሲገደል ብቻ የኖረው ሞት በዕለተ አርብ ግን "የሞት ሞቱ" በሆነው መድኃኒዓለም ክርስቶስ ኃይል ሞት እራሱ ፍግም ብሎ ሞቷል::

አሟሟቱ ደግሞ እንዲሁ አልነበረም "ከሞቱ አሟሟቱ "እንዲሉ አበው ሞት እንደ አረጀ አንበሳ ጥርሶቹ ረግፈው ጽኑ ሥቃይ ተሠቃይቶ ተዋርዶ በሆዱ ያለውን ሁሉ ተፍቶ ነበር የሞተው::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሞትን አሰቃቂ አሟሟት ከሆድ ሕመም ጋር ባመሳሰለበት "ተምሳሌተ መብል ወከርስ" ( Gasronomic Analogy ) እንዲህ ይገልፀዋል:-

      " የክርስቶስን ሰውነት በመቀበሉ ሞት ታላቅ ስኅተትን ሰራ:: ይህ ሰውነት በእርሱ የገዥነት ሥልጣን ሥር ያለ ተራ ሰውነት ኃጢያተኛ የሆነና የሚሞት ሰውነት መስሎት ነበር:: ከሰውነታቸው ጋር የማይስማማ ምግብን የበሉ ሰዎች ሲያስመልሳቸው የሚያወጡት አልስማማ ያላቸውን ምግብ ብቻ ሳይሆን የበሉትን ነገር ሁሉ ነው::

በሞትም ላይ የሆነው ይሔ ነው:: ሞት ፍፁም የማይሞት የሆነውን የክርስቶስን ሥጋ ዋጠ የማይሞተው ሕያው ክርስቶስ ለአልጠግብ ባዩ ሞትና ሲኦል የሚመር እና የማይስማማ ምግብ ሆነበት:: ሊስማማው ስላልቻለም ተፋው ከክርስቶስ ሥጋ ጋርም  ሲኦል ሆድ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ውጦ የያዘውን ሙት ሁሉ አብሮ ተፋ::

ለሞት የሚስማማ ብቸኛው ምግብ ኃጢያት ብቻ ነው:: ኃጢአት የሌለበት የጌታ ሰውነት ለሲኦል የማይስማማ ምግብ ነው:: ሞት ሊላመጥ የማይችል ትልቅ ድንጋይ ዋጠ ይህ ድንጋይ የማይላመጥ ብቻ ሳይሆን በሆድ ውስጥ ቆይቶ የሚያፈራርስና የሚሰባብር ነው::

ስለዚህ ሞት "የማዕዘን ድንጋይ" የሆነውን የክርስቶስን ፍፁም ቅዱስ የሆነን ሥጋ በዋጠ ጊዜ በታላቅ ስቃይና ድካም ውስጥ ሆኖ ጥንካሬዎቹን ሁሉ አጣ::

ለዚህም ነው ቅዱስ ጴጥሮስ "ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም" ያለው::

የትኛዋም ሴት ልጅ ለመውለድ ምጥን ባማጠች ጊዜ ሞት የክርስቶስን ሥጋ ይዞ የተጨነቀውን ያህል ተጨንቃ አታውቅም"

     "አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል" እንደሚባለው ሞት በአሟሟቱና በመዋረዱ የተነሣም እኛ ክርስቲያኖች እጅግ ንቀነው ሞት ሆይ "መውጊያህ የታለ?" እያልን እንዘብትበታለን::

ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታችን ትንሳዔው ይልቅ የሚያስደንቃት መሞቱ ነው:: ስለሞቱ "የማይሞተ ሞተ" ስትል ስለትንሳዔው ግን "የማነሳው ተነሳ" አትልም "ትንሳዔና ህይወት እኔ ነኝ" እንዳለው ትንሳዔ መነሳቱ ሕይወትም ሕያው መሆኑ ሊሆን የማይችል ክስተት አይደለም መሞቱ ግን አስደናቂ ነው::

የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ እያልን የምንቀድሰውም ስለዚህ ነው::

           ሕማማት ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ

“ሰሞች በሞታቸው ሀዘን ይጥሉብናል በሞቱ ህይወትን የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው::”

አብይ የማርያም ልጅ @jahABP ነኝ

መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንልን::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPG @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  2. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  4. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  5. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
  6. Jan 31, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #ቅዱስ_ዑራኤል_ሊቀ_መላዕክት #አባታችን😍😍🥰🥰 #ጥበብ__ሰጪው_መልዓክ #እ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →