ከሁሉም አብልጪ የምጠላው ነገር ውሸት ነው ውሸት እጠላለሁ በውሸት ብዙ ነገሮች ሲደበላለቁ አይቻለሁ ሰዎች ብዙ ሲታመሙ አይቻለው ትልልቅ ትዳሮች የረጅም ጊዜ ጟደኝነቶች የሚዋደድ ቤተሰብ ሲለያይ አይቻለሁ:: ስለዚህ ውሸት እጠላለሁ አዲስ ሰው ስተዋወቅ ከስሜ በፊት ማስቀድመው ውሸትን እንደምጠላ ያ ሰው ዋሽቶኝ ካገኝሁ መውደዴም ፍቅሬም ለሱ ያሉኝ ሀሳቦቼም እንደበፊቱ ለመሆን እንደሚቸግረኝ እንደማልችል ነው የምነግረው::
አደለም ዋሽቶኝ የዋሸኝ ከመሰልኝ ያንን ነገር እውነቱ ላይ ሳልደርስ በፍፁም አላቆምም እሱ እንኳን ሳያውቀው ነገሩን አጣራዋለሁ:: ውሸት ያመኛል የቀልድም ቢሆን የማታደርጉትን ነገር አትንገሩኝ አትበሉኝ ትንንሽ ውሸት ብላችሁ ምታስቧቸውንም ቢሆን እኔጋር ዋጋ አላቸው ሊያቆራጠን ይችላል:: ውይ አንተ ደግሞ አታካብድ ብትሉኝም ለኔ የውሸት ትንሽ የለውም የምትወደኝ ልታጣኝ የማትፈልግ ከሆነ በማንኛውም ሁኔታ ውጥም ቢሆን አትዋሸኝ:: እውነት መታወቁ አይቀርም......እኔም አጣርቼ እደርስበታለሁ ስለዚህ እንዳትዋሸኝ::
@jahABP ነኝ ይቀጥላል
Post #2240
532