TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2238 570
መጥፎ መሆን አልችልም ወይም ሰዎች ለሚበድሉኝ በደል ክፉ ምላሽ የለኝም.......ይልቁኑም አውቄ እንዳላወቀ የምሆንባቸው አያሌ ቀናት አሉ...ሰዎችን ክፉ በመመለስ ከክፉ ስራቸው እናስተምራቸዋለን የሚል እምነት የለኝም መልካም በመሆንና ጥሩውን በመመለስ ቀናውን በማሳየት ግን ከትላንት ስራቸው ተፀፅተው ዛሬን በይቅርታ ተሻግረነው ነገን በፍቅር እንድንኖራት ያደርገናል::

ደግሞ ዛሬ ባይሆንም ምናልባት አንድ ቀን መልካምነትን የህይወት መስመራቸው ያደርጉት ይሆናል.........

ሰዎች መጥፎ ማድረጋቸውን ከእኛ በላይ እራሳቸው ያውቁታልና ልንወቅሳቸው አይገባም እራሳቸው የሰሩት ስራ ሰላም ስለሚነሳቸው እሱ ህመም ብቻ በቂያቸው ነው እኔ ተጨማሪ ህመም ልሆንባቸው አልፈልግም:: ቀድሞውኑ ባይታመሙ ኖሮ በሰው ላይ ክፋትን ባላሰቡ ባልሰሩ ነበር::

ሰው ለሚሰጠኝ ነገሮች ፍቅርም ጥላቻም ቸልተኝነትም አልጨነቅም ሁሉንም እንደየ ፀባዩ ነው የማስተናግደው......እኔ ለምሰጣቸው ማንኛውም ነገሮች ግን እጠነቀቃለሁ ሁሌም ለሰዎች መልካም ነገር መስጠት አለብኝ ብዬ ነው የማስበው የደስታ ጊዜያቶች ካለባቸው ችግሮች አንዱን መቀነስን.........እኔ እኔ ስለሆንኩ የማደርጋችው መልካም ነገሮችን ነው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥም ቢሆን::
ሰውን መጥላት ቀላል ነገር ነው ከባዱ ነገር ሰውን መውደድ መቻል ነው የቅርብ የምንለውን ሰው ለመጥላት ብዙ ምክንያቶች አሉን አሁን ትልቁ የህይወት ጥያቄ ከዚህ መጥፎ ፀባዮች ውስጥ እንዴት ብለን ነው መልካሙን አጉልተን አንድን ሰው ለመውደድ የምንጠቀምበት ከመጥፎ ጎኑ ይልቅ መልካሙን አጉልተን የምናየው ነው????

ልክ ፈጣሪ ለኛ እንደሚያደርግልን ከብዙ መጥፎ ምግባራችን መልካሙን አይቶ እንደሚራራልን ለንሰሃ እድሜ እንደሚሰጠን::

3....4....5

@jahABP ነኝ በዋዜማው ጀባ ልበላችሁ......ይቀጥላል
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →