መኖር ጥሩ ነው ይኸው ስላለን ነው እዚ የደረስነው::
እዚህ ላደረሰኝ እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን::
ህይወት ቀጥቅጣ ቀጥቅጣ እሁን የሆንኩትን እኔ ሆኛለሁ ታላቁ ሰለሞን ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ ያለው እግዚአብሔር አምላክን በህይወት ካስግባ በኃላ ካለው ህይወቱ ጋር አስተያይቶት ነው እግዚአብሔር በህይወታችን ካለ የማንውጣው የማናሸንፈው ፈተና የለም ለዛም እኔ አንዱ ምስክር ነኝ:: መጋቢት 27 ዓለሙ በዳነበት ቀን በመወለዴ እድለኛ ነኝ::
የአምላክ እናት ጥበቃሽ ከብዙ ነገሮች ታድጎኛል የማያልፉ የመሰሉኝ እነዛን ቀናት ያላንቺ አጋዥነት እንዴት አልፋቸው ነበር ማን ያፅናናኝ ነበር እንዴት እወጣው ነበር አሁንም አንቺ ካለሽኝ ምን ማላልፈው ነገር አለ ህይወትሽ ትምህርት ቤቴ ነው:: አዛኝቱ ዘመኑ በቤቱ ይፈፀም ዘንድ ልጅሽን ለምኚልኝ የአንቺን ልመና ይሰማልና::
አሳዳጊዬ ቅዱስ ዑራዔል አሁንም ጥበቃህ አይለየኝ የጥበብ መልዓክ ነህና አሁንም ጥበብን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ሁሌም ክበርልኝከፍ ከፍ በልልኝ::
ከብዙ አመታት በፊት ያነበብኩት የአና ማስታወሻ መፅሐፍ ፀሐፊዋ በሳሏ አና ሰውን ለመጥላት በቂ ኧረ ከበቂ በላይ ምክንያት እያላት ግን እንዲ ትላለች "ሁኔታዎች እንጂ ሰዎች በተፈጥሮአቸው መልካም ናቸው ብዬ አስባለሁ" ትላለች:: በብዙ የሚጠሏት እሷን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቿን መላ አይሁዳውያንን እያሰቃዩ እያየች አንድ ኮርኒስ ውስጥ እንድትኖር አድርገዋት ነገሮች ናቸው እንጂ ሰዎች መጥፎዎች አይደሉም ትላለች:: ምን አይነት የይቅርታ ልብ ነው::
የጥንቱ ድንቁ መፅሐፍ ብርቅርቅርታ ዳንኤላ ስቲል ሰው የቱንም ያህል ችግር ውስጥ ቢሆን ማሸነፍ እንደሚችል አስተምሮኛል::
ዮቶር አለማየሁ ደመቀ እግዚአብሔር በህይወታችን መቼና በየት በኩል እንደሚመጣ እንደማናውቅ ለሚደርሱብን ችግሮቻችንም መፍትሔ እንደሚያዘጋጅልን አስተምሮኛል ከጥንካሬ ጋር በትግስት እሱን መጠበቅን ጭምር::
ታላቁ ሰውስራዎችህ ሁሌም ያስገርሙኛል ህይወታችንን በቋጠርካቸው ስንኞች ገልፀህልናል ኑር ባታምንም ለከንቱ አልተፈጠርክም ብለኸናል ወኪል ነሽ ከላይ ብለህ ፍቅርን ገልፅህልናል የደግነት ልኩ የሰውነት ውሃ ልክ ታላቁ ኤልያስ መልካ አከብርሃለሁ ከዚህም በልይ ብዙ የምትሰጠን ነገሮች ነበሩ ግን እራስህ እንዲ ብለህ ነበር "ኦ ምን አለፋኝ መልሱ ከጠፋኝ እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት የኔም እይን አይቷል እሱ ይበራው ሰሪ አይበልጥም ወይ ከተሰራው..."
ክፉ ሰዎች ጎድተውኝም ቢሆን እንዲህም አለ እንዴ እንድል አድርገው ህይወትን ቆም ብዬ እንዳስብ ጠንካራ አድርጋችሁኛል መልካም ሰዎች እንዳልወድቅ ደግፈው አቁመውኛል::
ጟደኞቼ ወንድሞቼ ቤተሰቦቼ ስላላችሁኝ እንዴት እድለኛ እንደሆንኩ 🥰🙏😍እግዚአብሔር ይጠብቅልኝ::
አንቺ መልካም ሴት አመሰግንሻለሁ😍
ቴሌግራም የሰጠኝ ተወዳጆቹ ጟደኞቼ እንደቤተሰቤ🙏🙏🙏
በዚች እድሜዬ ያነበብኳቸው መፅሐፍት እኔን ሰርተውኛል በስርዓት አንፀውኛል ለአሁን እኔነት ትልቅ ቦታ አላቸው::አንብብ ስታነብ እራስህን ትመለከታለህ ሌሎችን ሳይሆን እራስህን ለመውቀስ ድፍረቱን ታገኛለህ::
መንፈሳዊ መፅሐፍት ደግሞ ይበልጡኑ ወደፈጣሪ እንድትቀርብ ያደርጉሃል የቅዱሳን አባቶች ታሪክ ለህይወትህ ስንቅ ይሆንሃል ከእግዚአብሔር ጋር የማቻል ነገር እንደሌለ ይነግሩሃል::
(አባታችን አቡነ ሺኖዳ(ጉዞ ወደ እግዚአብሔር😍🥲😢)
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን(የእግዚአብሔር ትእግስት)
ዲ/ንግርማ ባቱ(ተርጟሚ)
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ
ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ....አመሰግናችኃለሁ😍🥰🙏🙏)
አያቴ ሁሉነገሬ ህይወት ያላንቺ ከባድ ነው::
መች እኔ እኖራለሁ እፍ ካላልሽብኝ የኔ የደግነት ጥግ የሰው መውደድ ልክ እወድሻለሁ የህይወቴ ቁልፏ አንቺ ነሽ::
26 ደስ የሚሉ አመታት መልካም ልደት ለእኔ😁😄😁🤪😜
Post #2241
620