TGViewer
Channel Public Channel
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

@fdredefenseforc

# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Subscribers
42.7K
Photos
42.1K
Videos
43
Links
11.7K
Recent Posts 10 shown
Post #59772 936
ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች የሠራዊቱን ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም አቅም በማጠናከር ውጤታማ ተልዕኮ ለመፈፀም ማሰልጠኛ ማዕከሉ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።

የምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደሳለው ብርሃኔ፣ ማሰልጠኛው የግዳጅ ቀጠናዎችን ሁኔታና የክፍሎችን የተግባር ፍላጎት መሠረት በማድረግ በተግባር የተደገፈ ጠንካራ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል።

ማሰልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናውን በማዕከሉ ብቻ ሳይገድብ ክፍሎች በግዳጅ ወደተሰማሩባቸው ቀጠናዎች በመድረስ በቀንና በሌሊት ተግባራዊ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።

በዚህም የዕዙ ክፍሎች የግዳጅ ሁኔታዎችን በተሻለ ዝግጁነት እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ፣ የሠራዊቱ ዲሲፕሊን፣ የቡድን ትስስርና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እንዲጎለብት አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።

ዕዙ በተጨማሪም በሐረሪ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የጸጥታ አባላትን በማሰልጠን የአካባቢውን የሰላምና የጸጥታ ሥራ ለማጠናከር ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል።
ዘገባው የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 11
  • 🥰 1
Post #59767 1.05K
ክፍለጦሩ 85 ሺህ ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019
ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ፈንቅል ክፍለጦር 85 ሺህ ብር በማዋጣት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ እና ሞጣ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ የመግዛት አቅም ለሌላቸው 100 ተማሪዎች 50 ደርዘን ደብተር እና 20 ፓኬት እስክሪብቶ እንዲሁም 200 እርሳስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ ገልፀዋል።

ባለፉት አመታት ፅንፈኛ ቡድኑ በፈጠረው ግጭት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ርቀው መቆየታቸውን ያወሱት ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ የተደረገው ድጋፍ 
በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህት ውጪ እንዳይሆኑ በማሰብ ነው ብለዋል።

ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው በክፍለጦሩ ለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ ደሱ ኦጌ
ፎቶግራፍ ሱራፌል እንድሪያስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 9
  • 👏 1
Post #59763 1.34K
የአካባቢው ህዝብና መስተዳደር  በግዳጅ ቀጠና በመገኘት ሠራዊቱን አበረታቱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም

የራያ ቆቦ ፣ የሃራ ከተማ መስተዳድር እና ነዋሪዎች በግንባር የሚገኘውን የሠራዊት አባላት ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመገኘት አበረታተው ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል።

ሰላም ጠሉ ህወሀት ወቅት እየጠበቀ የአካባቢያቸውን ሰላም መንሳትና ልማት ማደናቀፍ የተለመደ ተግባሩ መሆኑን የጠቀሱት የከተማው ነዋሪዎች እና  የመስተዳድር አካላት ተወካዮች የህወሀትን ትንኮሳ ለመመከት በሚደረገው ዘመቻ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልፀዋል።

ለሠራዊቱ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት ኬሎኔል  ደሳለኝ ደጉ የከተሞቹ ህብረተሰብና የመስተዳድር አካላቱ የቀንድ ከብቶችን ፣ ጁስ እና እሽግ ውሃዎችን ይዘው ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመምጣትና ለተዋጊው ኃይላችን በመደገፍ የሠራዊቱ ደጀን መሆናቸውን አረጋግጠዋል ብለዋል።

በተልዕኮዎቻችን ሁሉ የጥንካሬና የድል ባለቤትነታችን ምንጭ ህዝባችን ነው ያሉት ኃላፊው የህዝቡ ድጋፍና ማበረታቻ ሠራዊቱን ለሌላ የላቀ ድል የሚያነሳሳ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ዘግባው የሁንያለው ፈጠነ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • 👍 8
  • ❤ 4
Post #59758 1.24K
  • ❤ 1
  • 👍 1
Post #59757 1.64K
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ማህበራዊ ተሳትፎንና ሰራተኞችን የሚያበረታታ ተግባራትን አከናወነ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው “እኛው ለእኛው” አረጋውያንና ህፃናት መርጃ ማዕከል የአልባሳት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ለማዕከሉ ነዋሪዎችም  ማዕድ አጋርቷል።

በአየር ኃይል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮለሸኔል ቸኮለች ወንዳቸው አየር ኃይሉ ህዝብን ከመደገፍና ከማገልገል አኳያ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ ለማዕከሉ የተደረገው ድጋፍ ተቋሙ ከህዝብ ጎን መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል።

የማዕከሉ መስራችና ሊቀመንበር አቶ አሳምነው ደበላ በበኩላቸው፣ የአየር ኃይል አባላት በየዓመቱ ለማዕከሉ የሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ለተደረገው ድጋፍና የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ምስጋና አቅርበዋል።

በተቋሙ ውስጥም የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮችና መዝናኛ ክበቦች መምሪያ ለረጅም ዓመታት በትጋትና በቅንነት ላገለገሉ ሲቪል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል።

በመምሪያው ደረጃ በተዘጋጀው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ የመምሪያው ኃላፊ ኮሎኔል ንጉሴ ለማ ለሰራዊቱ አባላት፣ ለሲቪል ሰራተኞችና ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲሁም ሰራተኞችን የማበረታታት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብር ዋና ክፍል ኃላፊ ሻለቃ አማረ ዘገየ በበኩላቸው፣ ሽልማቱ በመደብሩ ለረጅም ዓመታት በትጋት ያገለገሉ ሰራተኞችን ለማበረታታትና ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

በመርሃ ግብሩ ለረጅም ዓመታት በተቋሙ ላገለገሉ የመደብር ዋና ክፍል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ ለመስቀል በዓል መዋያ የዶሮና የእንቁላል ስጦታም ተበርክቷል።

ዘጋቢ ፍቃዱ እሸቱ
ፎቶ ግራፍ ሰውነት ነጋሽ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 5
  • 👏 5
  • 👍 2
  • 😁 1
Post #59751 4.85K
ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፀጥታ ኃይሎች ለተውጣጡ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም

ለአራት ቀናት ለሽብርተኝነት የሲቭል- ወታደራዊ ምላሾች በሚል ርዕስ በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በዚሁ የስልጠና መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ወክለው በመካከላችን ስላለው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።

እኛ የምንሰራው ለሀገሮቻችን ነው ያሉት ኮሎኔል ማቲው  እኛ ለህግ የበላይነት እና ለሰብዓዊ መብቶች ዋጋ የምንሰጥ ሀገሮች ነን ሽብርተኞች ግን ለህግ የበላይነትና ለሰብዓዊ መብቶች አልፎም ለሰው ልጆች ህይወት ዋጋ አይሰጡም ብለዋል።

የወል ጠላታችን የሆነው ሽብርተኝነት እኛን ያጠናናል፤ በየቀኑ እናንተንም ያጠናችኋል ሲሉ የገለፁት ኮሎኔል ማቲው ጉዳት የማድረስ አቅሙን ማጥበብ የምንችለው አብረን ስንሰራ ነው ብለዋል ።

በመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የሁለትዮሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ሽዋቀና አማን በበኩላቸው በተለይም የጋራ የደህንነት ስጋቶችን ለመቋቋም የሚያስችል ተቋማዊ አቅምንና ትብብርን ለማጠናከር ላሳዩት ቀጣይነት ያለው አጋርነት፣ ሙያዊ ልምድ፣ ቴክኒካዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ኤምባሲ ፣ለአሜሪካ ወታደራዊ ቡድንና ለሁሉም ተሳታፊ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የዚህ ሥልጠና እውነተኛ ስኬት የሚለካው ያገኘናቸውን ትምህርቶች በየተቋሞቻችን ውስጥ ወደ ተግባራዊ መሻሻል እንዴት እንደምንለውጣቸው በሚለው ላይ  ነው ያሉት ኮሎኔል ሽዋቀና ሁሉም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ለባለደረቦቻቸው እንዲያካፍሉና ወደ ተግባርም በመተርጎም ሊሰሩበት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ከመከላከያ እና ከፀጥታ አካላት የተወጣጡት አባላት በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው አገራችንን ከሽብር ጥቃት እንዴት መከላከል እና ሽብርተኞችን በቀላሉ  መምታት የሚቻልበትን ሳይንሳዊ እዉቀት ቀስመናል ብለዋል።

ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶ ግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 38
  • 👍 18
  • 😁 3
  • 🔥 1
Post #59746 4.39K
  • ❤ 27
  • 👍 12
  • 🔥 2
Older posts →

About this channel

How can I read @fdredefenseforc without a Telegram account?
TGViewer shows the public web preview Telegram publishes for FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት: recent posts, photos, videos and the subscriber count, with no app, login or account.
How many subscribers does FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት have?
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (@fdredefenseforc) has 42.7K subscribers on Telegram, refreshed roughly every 30 minutes.
Does FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት know I viewed it here?
No. Public channel previews carry no viewer identity, and TGViewer has no accounts or tracking of what you look up.
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →