ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም
የምስራቅ ዕዝ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች የሠራዊቱን ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም አቅም በማጠናከር ውጤታማ ተልዕኮ ለመፈፀም ማሰልጠኛ ማዕከሉ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።
የምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደሳለው ብርሃኔ፣ ማሰልጠኛው የግዳጅ ቀጠናዎችን ሁኔታና የክፍሎችን የተግባር ፍላጎት መሠረት በማድረግ በተግባር የተደገፈ ጠንካራ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል።
ማሰልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናውን በማዕከሉ ብቻ ሳይገድብ ክፍሎች በግዳጅ ወደተሰማሩባቸው ቀጠናዎች በመድረስ በቀንና በሌሊት ተግባራዊ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።
በዚህም የዕዙ ክፍሎች የግዳጅ ሁኔታዎችን በተሻለ ዝግጁነት እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ፣ የሠራዊቱ ዲሲፕሊን፣ የቡድን ትስስርና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እንዲጎለብት አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።
ዕዙ በተጨማሪም በሐረሪ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የጸጥታ አባላትን በማሰልጠን የአካባቢውን የሰላምና የጸጥታ ሥራ ለማጠናከር ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል።
ዘገባው የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Post #59772
3.68K
- ❤ 20
- 👍 6
- 🥰 2