TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59767 3.94K
ክፍለጦሩ 85 ሺህ ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019
ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ፈንቅል ክፍለጦር 85 ሺህ ብር በማዋጣት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ እና ሞጣ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ የመግዛት አቅም ለሌላቸው 100 ተማሪዎች 50 ደርዘን ደብተር እና 20 ፓኬት እስክሪብቶ እንዲሁም 200 እርሳስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ ገልፀዋል።

ባለፉት አመታት ፅንፈኛ ቡድኑ በፈጠረው ግጭት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ርቀው መቆየታቸውን ያወሱት ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ የተደረገው ድጋፍ 
በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህት ውጪ እንዳይሆኑ በማሰብ ነው ብለዋል።

ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው በክፍለጦሩ ለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ ደሱ ኦጌ
ፎቶግራፍ ሱራፌል እንድሪያስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 22
  • 👏 4
  • 👍 2
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 26, 2026የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ለሚገኘው ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በደሴና አካባቢው…
  2. Sep 26, 2026photo post
  3. Sep 26, 2026ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ…
  4. Sep 26, 2026photo post
  5. Sep 26, 2026photo post
  6. Sep 26, 2026የአካባቢው ህዝብና መስተዳደር በግዳጅ ቀጠና በመገኘት ሠራዊቱን አበረታቱ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የራያ ቆ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →