TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59763 3.88K
የአካባቢው ህዝብና መስተዳደር  በግዳጅ ቀጠና በመገኘት ሠራዊቱን አበረታቱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም

የራያ ቆቦ ፣ የሃራ ከተማ መስተዳድር እና ነዋሪዎች በግንባር የሚገኘውን የሠራዊት አባላት ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመገኘት አበረታተው ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል።

ሰላም ጠሉ ህወሀት ወቅት እየጠበቀ የአካባቢያቸውን ሰላም መንሳትና ልማት ማደናቀፍ የተለመደ ተግባሩ መሆኑን የጠቀሱት የከተማው ነዋሪዎች እና  የመስተዳድር አካላት ተወካዮች የህወሀትን ትንኮሳ ለመመከት በሚደረገው ዘመቻ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልፀዋል።

ለሠራዊቱ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት ኬሎኔል  ደሳለኝ ደጉ የከተሞቹ ህብረተሰብና የመስተዳድር አካላቱ የቀንድ ከብቶችን ፣ ጁስ እና እሽግ ውሃዎችን ይዘው ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመምጣትና ለተዋጊው ኃይላችን በመደገፍ የሠራዊቱ ደጀን መሆናቸውን አረጋግጠዋል ብለዋል።

በተልዕኮዎቻችን ሁሉ የጥንካሬና የድል ባለቤትነታችን ምንጭ ህዝባችን ነው ያሉት ኃላፊው የህዝቡ ድጋፍና ማበረታቻ ሠራዊቱን ለሌላ የላቀ ድል የሚያነሳሳ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ዘግባው የሁንያለው ፈጠነ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 16
  • 👍 15
  • 😁 1
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 26, 2026የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ለሚገኘው ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በደሴና አካባቢው…
  2. Sep 26, 2026photo post
  3. Sep 26, 2026ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ…
  4. Sep 26, 2026photo post
  5. Sep 26, 2026ክፍለጦሩ 85 ሺህ ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የ6ኛ ዕዝ ፈንቅል…
  6. Sep 26, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →