የኢትዮጵያ አየር ኃይል ማህበራዊ ተሳትፎንና ሰራተኞችን የሚያበረታታ ተግባራትን አከናወነ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም
የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው “እኛው ለእኛው” አረጋውያንና ህፃናት መርጃ ማዕከል የአልባሳት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ለማዕከሉ ነዋሪዎችም ማዕድ አጋርቷል።
በአየር ኃይል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮለሸኔል ቸኮለች ወንዳቸው አየር ኃይሉ ህዝብን ከመደገፍና ከማገልገል አኳያ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ ለማዕከሉ የተደረገው ድጋፍ ተቋሙ ከህዝብ ጎን መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል።
የማዕከሉ መስራችና ሊቀመንበር አቶ አሳምነው ደበላ በበኩላቸው፣ የአየር ኃይል አባላት በየዓመቱ ለማዕከሉ የሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ለተደረገው ድጋፍና የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ምስጋና አቅርበዋል።
በተቋሙ ውስጥም የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮችና መዝናኛ ክበቦች መምሪያ ለረጅም ዓመታት በትጋትና በቅንነት ላገለገሉ ሲቪል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል።
በመምሪያው ደረጃ በተዘጋጀው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ የመምሪያው ኃላፊ ኮሎኔል ንጉሴ ለማ ለሰራዊቱ አባላት፣ ለሲቪል ሰራተኞችና ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲሁም ሰራተኞችን የማበረታታት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብር ዋና ክፍል ኃላፊ ሻለቃ አማረ ዘገየ በበኩላቸው፣ ሽልማቱ በመደብሩ ለረጅም ዓመታት በትጋት ያገለገሉ ሰራተኞችን ለማበረታታትና ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ ለረጅም ዓመታት በተቋሙ ላገለገሉ የመደብር ዋና ክፍል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ ለመስቀል በዓል መዋያ የዶሮና የእንቁላል ስጦታም ተበርክቷል።
ዘጋቢ ፍቃዱ እሸቱ
ፎቶ ግራፍ ሰውነት ነጋሽ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Post #59757
2.16K
- ❤ 8
- 👏 7
- 👍 3
- 😁 1