ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፀጥታ ኃይሎች ለተውጣጡ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም
ለአራት ቀናት ለሽብርተኝነት የሲቭል- ወታደራዊ ምላሾች በሚል ርዕስ በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
በዚሁ የስልጠና መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ወክለው በመካከላችን ስላለው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።
እኛ የምንሰራው ለሀገሮቻችን ነው ያሉት ኮሎኔል ማቲው እኛ ለህግ የበላይነት እና ለሰብዓዊ መብቶች ዋጋ የምንሰጥ ሀገሮች ነን ሽብርተኞች ግን ለህግ የበላይነትና ለሰብዓዊ መብቶች አልፎም ለሰው ልጆች ህይወት ዋጋ አይሰጡም ብለዋል።
የወል ጠላታችን የሆነው ሽብርተኝነት እኛን ያጠናናል፤ በየቀኑ እናንተንም ያጠናችኋል ሲሉ የገለፁት ኮሎኔል ማቲው ጉዳት የማድረስ አቅሙን ማጥበብ የምንችለው አብረን ስንሰራ ነው ብለዋል ።
በመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የሁለትዮሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ሽዋቀና አማን በበኩላቸው በተለይም የጋራ የደህንነት ስጋቶችን ለመቋቋም የሚያስችል ተቋማዊ አቅምንና ትብብርን ለማጠናከር ላሳዩት ቀጣይነት ያለው አጋርነት፣ ሙያዊ ልምድ፣ ቴክኒካዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ኤምባሲ ፣ለአሜሪካ ወታደራዊ ቡድንና ለሁሉም ተሳታፊ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የዚህ ሥልጠና እውነተኛ ስኬት የሚለካው ያገኘናቸውን ትምህርቶች በየተቋሞቻችን ውስጥ ወደ ተግባራዊ መሻሻል እንዴት እንደምንለውጣቸው በሚለው ላይ ነው ያሉት ኮሎኔል ሽዋቀና ሁሉም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ለባለደረቦቻቸው እንዲያካፍሉና ወደ ተግባርም በመተርጎም ሊሰሩበት እንደሚገባ ገልፀዋል ።
ከመከላከያ እና ከፀጥታ አካላት የተወጣጡት አባላት በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው አገራችንን ከሽብር ጥቃት እንዴት መከላከል እና ሽብርተኞችን በቀላሉ መምታት የሚቻልበትን ሳይንሳዊ እዉቀት ቀስመናል ብለዋል።
ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶ ግራፍ ገነት አወቀ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Post #59751
5.01K
- ❤ 39
- 👍 19
- 😁 3
- 🔥 1