TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #2475 · Back to latest

Older Posts 15 shown
Post #2473 454
B PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryamlej
#እንኳን_አደረሳችሁ
#ከተራ💚💛❤ #ተናፋቂው ቀን
#መድሃኒአለም_የነገስታት_ሁሉ_ንጉስ✔️
#ወላዲተ_አምላክ_ድንግል_ማርያም_አትለየን
#መልዓኩ_ቅዱስ_ዑራኤል😍😍😍 የኛ አባት
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ፃድቁ_አባታችን_አቡዬ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ተክለሃይማኖት


#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን

#street_photography

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Post #2472 460
B PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryamlej
#እንኳን_አደረሳችሁ
#ከተራ💚💛❤ #ተናፋቂው ቀን
#መድሃኒአለም_የነገስታት_ሁሉ_ንጉስ✔️
#ወላዲተ_አምላክ_ድንግል_ማርያም_አትለየን
#መልዓኩ_ቅዱስ_ዑራኤል😍😍😍 የኛ አባት
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ፃድቁ_አባታችን_አቡዬ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ተክለሃይማኖት


#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን

#street_photography

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Post #2471 442
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ


እነሆ ከተናፋቂው ቀን ያነሳኃቸው ፎቶዎች ተጋበዙልኝ🏃🏿🏃🏿🏃🏿🏃🏿



እንኳን ለከተራ በዓል አደረሳችሁ😍🙏😍


በትዕግስት ጠብቁኝ
Post #2470 638
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN

#ምፅዋት_ሙት_ታስነሳለች


ምጽዋት ሥርየት ሀጢያትን ትሰጣለች:: ሞትንም ቢኾን ታርቃለች ይህስ እንደምንድነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልፅ አደርግልሃለሁ::

"መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ??" ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል:: ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅልህ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውነት ከተደረገ ታሪክ ተነስቼ እነግርሃለሁ....የምነግርህን ነገር አትጠራጠር........

#ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች:: መልካምን ሥራን የሞላባትና ምፅዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታዘጋጅ ነበረች:: ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ትሰጣቸው ነበር:: ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች::

አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛውሰዓት ብድርታቸውን እንደከፈሉ ተመልከት:: መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ #ቅዱስ_ጴጥሮስ ኼዱ:: ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስና ሌላውን ሁሉ አሳዩት::


ከእነርሱ ጋር በህይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደነበር ነገሩት:: እንደእናትም የምትሆንላቸውን እንዳጡ አልቅሰው ነገሩት ስለእነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት::

የተወደደ ጴጥሮስም ምን አደረገ?? "ኹሉን ወደ ውጪ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ:: ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ '#ጣቢታ_ሆይ_ተነሺ' አላት::
እርስዋም አይኗን ከፈተች:: ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች:: እጁንም ለእርስዋ ሰጥቷት አስነሳት:: ምእመናንና መበለቶችን ጠራ:: ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት"(ሐዋ 9:40-42)

የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርይው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህ?? በወዲያው አለምስ ተወውና በዚህ ዓለም ኑሮ ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደተቀበልች ተገነዝብክን?? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን?

እርስዋ ምግብን ልብስን ሰጠቻቸው እነርሱ ግን ከሞት ወደ ህይወት እንድትመጣ አደረጟት:: ለመበለቶቹም ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት::

እንግዲህ ምፅዋት የመድኃኒቷን ኃይል ተመለከትህ?

እንግዲያውስ እኛም ይህን መድሃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ:: መድሃኒቱ ይህንን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ:: ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ::

መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይሆን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ::

አንድ ሰው እንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቆጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ::


#መበለቶች_እንደ_ጣቢታ_ከሞተ_ነፍስ_ይታደጉን_ዘንድ_ይህን_መድኃኒት_ከእነርሱ_እንግዛ:::

+ + +



ይለናል ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች_እና_ሌሎች ከሚለው መፅሐፉ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2469 542
ምፅዋት ሙት ታስነሳለች


ምጽዋት ሥርየት ሀጢያትን ትሰጣለች:: ሞትንም ቢኾን ታርቃለች ይህስ እንደምንድነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልፅ አደርግልሃለሁ::

"መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ??" ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል:: ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅልህ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውነት ከተደረገ ታሪክ ተነስቼ እነግርሃለሁ....የምነግርህን ነገር አትጠራጠር........



ይለናል ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


4:00 ይጠብቁኝ አብይ የማርያም ልጅ ነኝ::
Post #2467 635
AB PHOTOGRAPHY & Graphic Design

ጌታ_ያልተውለደበት_ስፍራ

ጌታን ለመውለድ የቀረበችውን ድንግል ማርያምና ዮሴፍ ምሽት ማደሪይ ፍለጋ ሲንከራተቱ ቆይተው ማደርያ ፍለጋ ሲንከራተቱ ቆይተው ነበር:: ወደ አንድ እንግዶች ማደሪያ ቤት ሔደው ሲጠይቁ ቦታ የለንም ብለው ከበር መለሱአቸው::

ስለዚህ ዮሴፍና ድንግል ማርያም ያንን የእንግዶች ማረፊያ ትተው ወደ ከብቶች በረት ገሰገሱ:: በዚያ ግርግም ውስጥም የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ ተወለደ::

እስኪ ዛሬ ለከብቶቹ በረት '' በጎል ሰከበ''(በበረት ተኛ) እያልን መዘመራችንን ትተን ጌታ ላልተወለደባት የእንግዶች ማደሪያ ሥፍራ ትንሽ አብረን እናልቅስለት:: በዓለማችን እጅግ ዕድለ ቢስ ስለሆነው ስለዚያ ቤት ጥቂ ሙሾ እናውርድ::

የዚያ ባለቤቶች ያንን ለሊት ከደጃፋቸው የቆመችው አንዲት ልትወልድ የተቃረበች ወጣት ነበረች:: 'ቦታ የለንም' ብለው ሲመልሱአት ምንም አልመሰላቸውም ትንሽ እንኳን ቅር አላላቸውም ነበር:: በማኅፀንዋ ያለው ጨለማውን ዓለም የሚያበራ ፀሀይ የዓለምን ጥም የሚያረካ ውኃ በደሙ አለምን የሚያጥብ መድኃኒት እንደሆነ አላወቁም ነበርና '' ቦታ የለንም '' አሉ::

እናንተ የአለማችን እድለቢስ ሰዎች ሆይ ያቺን ምሽት ማንን ከበር እንደመለሳችሁ እስኪ እኔ ልንገራችሁ::

ከበር የቆመችው ማን እንድሆነች በማህፀኗ የያዘችው ማን እንደሆነ ብታውቁ ኖሮ ቀድማችሁ ያስገባችሁዋቸውን እንግዶች ሁሉ ''በህግ አምላክ ውጡልን'' ብላችሁ ማስወጣታችሁ አይቀርም ነበርና ትሰሙ እንደሆን እኔ ልንገራችሁ:: ብታውቁአት ኖሮ እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት....

''የጌታችን እናት ወደ እኛ ትመጪ ዘንድ እኛ ምን ነን?'' ተትሏት ነበር::
እናንተ የእንግዶች ማደሪያ ባለቤቶች ሆይ! እርግጥ ነው እናንተ ከበር የመለሳችሁት እንዲት የፀነሰች የገሊላ ናዝሬት እንግዳ ብቻ ነበር::

ለእርስዋ ቦታ የለም ብሎ መናገርም ቀላል ነገር መስሎአችሁ ሊሆን ይችላል::

እመኑኝ ለእርስዋ ''አንቺን ለማሳደር ቦታ የለንም'
ስትሉአት ግን ማንን እንደመለሳችሁት አላወቅችሁም:: እርግጥ ነው ቦታው በእንግዳ ተይዟል ትሉኝ ይሆናል:: ግን ደሞ ለመውለድ ለተቃረበች ወጣት ሥፍራ ቢጠፋ እንኳን የራስም አልጋ ቢሆን መልቀቅ አይገባም ነበር?
ለአንዲት ለምትወልድ እናት ቸርነት ምድረግ ሰብአዊ ግዴታ አይደለምን? ብታደርጉ ኖሮ የምታገኙትን ከጠበቃችሁት በላይ በሆነ ነበር::

እርስዋን ብታስገቧት ኖሮ የሰማይና ምድሩ ንጉስ ኢየሱስ ከቤታችሁ ይገባ ነበር:: በቤታችሁ ውስጥ ከምድር እስከሰማይ የሚደርስ መሰላል ተዘርግቶ እልፍኛችሁ በመላዕክት ዝማሬ በእረኞች ደስታ በሰብአ ሰገል ስጦታ ይጥለቀለቅ ነበር:: እናንተም ከሞታችሁ በኃላ ጭምር ለዘመናት እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ የዓለም ህዝብ እየመጣ የቤታችችሁን ወለል ይስም በደጃፋችሁም ይንከባለል ነበር::

#አቤት_ድንግል_ማርያምን '' #ቦታ_የለንም'' ብሎ ከደጅ መመለስ የሚያስከፍለው ዋጋ የሚያሳጣው ጸጋ እንዴት ያለ ነው?! ምነው እንደ እናንተ በዚያ ዘመን በኖርኩና ድንግል ማርያምን ከደጄ ቆማ አግኝቻት ከአልጋዬ ወርጄ በተቀበልኳት!

#እመኑኝ_ለማርያም_ቦታ_የለኝም_ያለ_ሰው_ቦታ_ያጣ_ለኢየሱስ_ነው::

እርሷን ወደ ቤቱ ግቢ ያላት ሰው ግን ጌታን ወደቤቱ ያስገባዋል::

#ጌታ_ያለው_ደሞ_ሁሉም_አለው::

አይ እናንተዬ! ሌላ እንግዳ ከምታግበሰብሱ ለአንዲት ድንግል ቦታብትሰጡአት ኖሮ ቤታችሁ ሰማይ ይሆን ነበር::

#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሄኖክ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ


#መልካም_የልደት_በዓል_ይሁንልን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2466 488
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የጌታን ልደት እንዴት ልታከብረው አሰብከው??

ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት ስም ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከስም በላይ የሆነ ስም ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም አጋንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም ሙታንን የሚያስነሳ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲ ብሎ ተፅፉል::............

#ኢየሱስ
አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሰራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትፅፈው ብዕርህ አልተስበረም ወይ?? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ እልተንቀጠቀጡም ወይ??

ጌታችን በዚያ መዝገብ ላይ ተፃፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተፅፉት ንፅህት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተፅፈዋል:: #ጥሩ_ሰዎች #ክፉ_ሰዎች #ውንጀለኞች #ነፍሰ_ገዳዮች #ሰካራሞች #አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተፅፎአል::

ክርስቶስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በህይወት ዘመኑ የኃጢያተኞች ወዳጅ የሚል ቅፅል ስም ወጣለት ጌታ በልደቱ ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ::

#እኛን_ከቅዱሳን_ጋር_ሊደምረን_እሱ_ከኃጢአተኞች_ጋር_ተቆጠረ::

#አንተ_ስለእርሱ_ከንፁሐን_ጋር_ተቆጠርለት::
በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ::


#እስኪ_እንተ_ልደቱን_አስበህ #ከሚስክሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: #ከዘራፊዎች መካከል ተለይ:: #ከዝሙተኞች ማህበር ውጣ ክርስቶስን ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው::
ወደ ሞት የገባው ሙታን ሊያወጣ ነው::
ወደ ሲዖል የወረደው ነፍሳትን ከሲዖል ሊይወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የህዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንንም በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊይስወጣን ነው::

''ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተፃፈ ደስ ይበላችሁ'' ሉቃ 10:

#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሄኖክ

ሙሉ ገቢው #ለደብረ_አሚን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ቤተ ክርስትያን የሕንፃ እድሳት ሥራ የሚውል ነውና ሁላችንም ይህን መፅሐፍ በመግዛት አሻራችንን እናሳልፍ ከመፅሐፉም እውቀትን እንሸምት እላለሁ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2464 460
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ለምን_ትቀናለህ

በዜና አበው ላይ አጋንት አንድ መነኩሴን ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተፅፏል:: መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረስ መናኝ ነበር:: የአጋንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ::

ተራ በተራ ወደሱ እየሔዱ የፈተናን ወጥመዳቸውን ዘረጉበት:: በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ አልተሳካም በምግብም ሞከሩ ድል ነሳቸው:: የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየመንገድ እየተገለፁ አንዴ ሰው መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም::

አለቃቸው ይሔን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ:: በጆሮው የሆነ ነገር ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ:: ይህን ጊዜ አጋንቱ እያዩትመነኩሴው መንፈሳዊ ገፅታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት::

በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት:: እርሱም እንዲህ አላቸው:- ''ከአንተ ጋር ያደገው ከአንተ ጋር የተማረው ጟደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው'' አላቸው አጋንቱ በደስታ ጨፈሩ::

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል:: መፅሐፈ ቅዳሴ #ሞትን ሲገልፀው '#በሰይጣን_ቅናት_ወደ_አለም_የገባ' ይለዋል:: ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲምኙ አድርጎ ዓለም ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙ ሺዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት::

መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆነ አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን::

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር::
#በምድር_ላይ_እግዚአብሔር_የፈጠረው_አትን_የሚመስል_ሌላ_ሰው_የለም::
#ካንተ_ቀድሞም_በትክክል_አንተን_የሆነ_ሰው_አልተፈጠረም_ለወደፊትም_አይፈጠርም::
#እግዚአብሔር_ቀድሞ_ያልሰራው_ደግሞም_የማይሰራው_ምርጥ_ዕቃው_ነህና_ርስህን_ከሌሎች_ጋር_አታወዳድር::

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ:: ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተ ውስጥ ነው:: ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ::

#መብለጥ_ከፈለክም_አሁን_ያለውን_ራስህን_ብለጠውና_ሌላ_ትልቅ_አንተን_ሁን::

#ቅናት_እጅግ_ክፉ_ኃጢያት_ነው:: ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: #ቅናት_ግን_በምታስተውል_ነፍሱ_ውስጥ_የሚበቅል_መርዝ_ነው::

ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር:: የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ::

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎች ሰዎችንም ውደዳቸው:: ከወደድሃቸው 'ፍቅር አይቀናም'ና የቅናት ስሜት ሲሰማህ 'ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ' ብለህ ለምነው::

'በአገባብ እንመላለስ በዘፈንና በስካር አይሁን በዝሙትና በመዳራት አይሁን በክርክር በቅናት አይሁን' ሮሜ 13:13



#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሄኖክ

ሙሉ ገቢው #ለደብረ_አሚን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ቤተ ክርስትያን የሕንፃ እድሳት ሥራ የሚውል ነውና ሁላችንም ይህን መፅሐፍ በመግዛት አሻራችንን እናሳልፍ ከመፅሐፉም እውቀትን እንሸምት እላለሁ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት መልካም ጊዜ::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2458 427
AB PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryamlej
#ኦርቶዶክሳዊ_ወጣት 😍😍😍😍😍
#እንኳን_አደረሳችሁ


#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ


#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን

#street_photography

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Post #2457 557
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ዘኪዎስ_አጭር_ባይሆን_ኖሮ

ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት::
የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም::
#ጌታ_ሊታዩ_ከሚሞክሩት_ይልቅ_ሊያዩት_የሚሹትን_ይወዳልና_ዘኪዎስን_ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: 'ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል' አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኪዮስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋርእየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኪዎስ አጭር_ባይሆን_ከዛፍ_ላይ_አይወጣም_ነበር::
አጭር ባይሆን የሠራዊትአምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር::

በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉስ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሊያሳንሰው ነበር::
በምድር በመፅሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ....

#እግዚአብሔር_ለነፍሳችን_መዳን_የሚያሳጥርብን_ብዙነ_ገር_አለ::

እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥር ነገር ግን አይጠፋም::

ይሔ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እነሱን ማለቴ ነው:: ይሄ ይጎድልብኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::

#እጥረትህ_መክበሪያህ_ነው::
#ጉድለትህም_መዳኛህ_ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያት ይሁንህ::
በጉድለትህ እንደዘኪዎስ ከፍ በልበት::

ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም:: ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል::

#ከዚያም_ስላጠረህ_ስለጎደለብህ_ነግር_ፈጣሪን_ስታመሰግነው_ትኖራለህ::

#እመነኝ_አንዳንድ_ጉድለቶች_እድሎች_ናቸው::

ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ግንቦት 23 2014
አዲስ አበባ

#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሔኖክ_ኃይሌ

ሙሉ ገቢው #ለደብረ_አሚን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ቤተ ክርስትያን የሕንፃ እድሳት ሥራ የሚውል ነውና ሁላችንም ይህን መፅሐፍ በመግዛት አሻራችንን እናሳልፍ ከመፅሐፉም እውቀትን እንሸምት እላለሁ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2455 440
AB PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryamlej
#ቅዱስ_እምነቱን_ቤቴ_ነስንሼ
ተነሳው በክብር ፅጋን አፍሼ
በእግሮቹ ፍኖት ልጁ ተራመድኩ
ገድል ታምሩን እየመሰከርኩ::

#እንኳን_አደረሳችሁ

#መድሐኒዓለም_የነገስታት_ሁሉ_ንጉስ


#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ


#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን

#street_photography

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →