TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2470 638
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN

#ምፅዋት_ሙት_ታስነሳለች


ምጽዋት ሥርየት ሀጢያትን ትሰጣለች:: ሞትንም ቢኾን ታርቃለች ይህስ እንደምንድነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልፅ አደርግልሃለሁ::

"መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ??" ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል:: ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅልህ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውነት ከተደረገ ታሪክ ተነስቼ እነግርሃለሁ....የምነግርህን ነገር አትጠራጠር........

#ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች:: መልካምን ሥራን የሞላባትና ምፅዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታዘጋጅ ነበረች:: ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ትሰጣቸው ነበር:: ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች::

አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛውሰዓት ብድርታቸውን እንደከፈሉ ተመልከት:: መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ #ቅዱስ_ጴጥሮስ ኼዱ:: ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስና ሌላውን ሁሉ አሳዩት::


ከእነርሱ ጋር በህይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደነበር ነገሩት:: እንደእናትም የምትሆንላቸውን እንዳጡ አልቅሰው ነገሩት ስለእነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት::

የተወደደ ጴጥሮስም ምን አደረገ?? "ኹሉን ወደ ውጪ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ:: ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ '#ጣቢታ_ሆይ_ተነሺ' አላት::
እርስዋም አይኗን ከፈተች:: ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች:: እጁንም ለእርስዋ ሰጥቷት አስነሳት:: ምእመናንና መበለቶችን ጠራ:: ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት"(ሐዋ 9:40-42)

የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርይው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህ?? በወዲያው አለምስ ተወውና በዚህ ዓለም ኑሮ ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደተቀበልች ተገነዝብክን?? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን?

እርስዋ ምግብን ልብስን ሰጠቻቸው እነርሱ ግን ከሞት ወደ ህይወት እንድትመጣ አደረጟት:: ለመበለቶቹም ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት::

እንግዲህ ምፅዋት የመድኃኒቷን ኃይል ተመለከትህ?

እንግዲያውስ እኛም ይህን መድሃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ:: መድሃኒቱ ይህንን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ:: ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ::

መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይሆን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ::

አንድ ሰው እንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቆጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ::


#መበለቶች_እንደ_ጣቢታ_ከሞተ_ነፍስ_ይታደጉን_ዘንድ_ይህን_መድኃኒት_ከእነርሱ_እንግዛ:::

+ + +



ይለናል ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች_እና_ሌሎች ከሚለው መፅሐፉ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →