TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2464 460
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ለምን_ትቀናለህ

በዜና አበው ላይ አጋንት አንድ መነኩሴን ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተፅፏል:: መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረስ መናኝ ነበር:: የአጋንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ::

ተራ በተራ ወደሱ እየሔዱ የፈተናን ወጥመዳቸውን ዘረጉበት:: በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ አልተሳካም በምግብም ሞከሩ ድል ነሳቸው:: የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየመንገድ እየተገለፁ አንዴ ሰው መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም::

አለቃቸው ይሔን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ:: በጆሮው የሆነ ነገር ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ:: ይህን ጊዜ አጋንቱ እያዩትመነኩሴው መንፈሳዊ ገፅታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት::

በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት:: እርሱም እንዲህ አላቸው:- ''ከአንተ ጋር ያደገው ከአንተ ጋር የተማረው ጟደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው'' አላቸው አጋንቱ በደስታ ጨፈሩ::

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል:: መፅሐፈ ቅዳሴ #ሞትን ሲገልፀው '#በሰይጣን_ቅናት_ወደ_አለም_የገባ' ይለዋል:: ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲምኙ አድርጎ ዓለም ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙ ሺዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት::

መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆነ አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን::

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር::
#በምድር_ላይ_እግዚአብሔር_የፈጠረው_አትን_የሚመስል_ሌላ_ሰው_የለም::
#ካንተ_ቀድሞም_በትክክል_አንተን_የሆነ_ሰው_አልተፈጠረም_ለወደፊትም_አይፈጠርም::
#እግዚአብሔር_ቀድሞ_ያልሰራው_ደግሞም_የማይሰራው_ምርጥ_ዕቃው_ነህና_ርስህን_ከሌሎች_ጋር_አታወዳድር::

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ:: ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተ ውስጥ ነው:: ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ::

#መብለጥ_ከፈለክም_አሁን_ያለውን_ራስህን_ብለጠውና_ሌላ_ትልቅ_አንተን_ሁን::

#ቅናት_እጅግ_ክፉ_ኃጢያት_ነው:: ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: #ቅናት_ግን_በምታስተውል_ነፍሱ_ውስጥ_የሚበቅል_መርዝ_ነው::

ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር:: የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ::

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎች ሰዎችንም ውደዳቸው:: ከወደድሃቸው 'ፍቅር አይቀናም'ና የቅናት ስሜት ሲሰማህ 'ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ' ብለህ ለምነው::

'በአገባብ እንመላለስ በዘፈንና በስካር አይሁን በዝሙትና በመዳራት አይሁን በክርክር በቅናት አይሁን' ሮሜ 13:13



#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሄኖክ

ሙሉ ገቢው #ለደብረ_አሚን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ቤተ ክርስትያን የሕንፃ እድሳት ሥራ የሚውል ነውና ሁላችንም ይህን መፅሐፍ በመግዛት አሻራችንን እናሳልፍ ከመፅሐፉም እውቀትን እንሸምት እላለሁ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት መልካም ጊዜ::

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →