TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2467 635
AB PHOTOGRAPHY & Graphic Design

ጌታ_ያልተውለደበት_ስፍራ

ጌታን ለመውለድ የቀረበችውን ድንግል ማርያምና ዮሴፍ ምሽት ማደሪይ ፍለጋ ሲንከራተቱ ቆይተው ማደርያ ፍለጋ ሲንከራተቱ ቆይተው ነበር:: ወደ አንድ እንግዶች ማደሪያ ቤት ሔደው ሲጠይቁ ቦታ የለንም ብለው ከበር መለሱአቸው::

ስለዚህ ዮሴፍና ድንግል ማርያም ያንን የእንግዶች ማረፊያ ትተው ወደ ከብቶች በረት ገሰገሱ:: በዚያ ግርግም ውስጥም የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ ተወለደ::

እስኪ ዛሬ ለከብቶቹ በረት '' በጎል ሰከበ''(በበረት ተኛ) እያልን መዘመራችንን ትተን ጌታ ላልተወለደባት የእንግዶች ማደሪያ ሥፍራ ትንሽ አብረን እናልቅስለት:: በዓለማችን እጅግ ዕድለ ቢስ ስለሆነው ስለዚያ ቤት ጥቂ ሙሾ እናውርድ::

የዚያ ባለቤቶች ያንን ለሊት ከደጃፋቸው የቆመችው አንዲት ልትወልድ የተቃረበች ወጣት ነበረች:: 'ቦታ የለንም' ብለው ሲመልሱአት ምንም አልመሰላቸውም ትንሽ እንኳን ቅር አላላቸውም ነበር:: በማኅፀንዋ ያለው ጨለማውን ዓለም የሚያበራ ፀሀይ የዓለምን ጥም የሚያረካ ውኃ በደሙ አለምን የሚያጥብ መድኃኒት እንደሆነ አላወቁም ነበርና '' ቦታ የለንም '' አሉ::

እናንተ የአለማችን እድለቢስ ሰዎች ሆይ ያቺን ምሽት ማንን ከበር እንደመለሳችሁ እስኪ እኔ ልንገራችሁ::

ከበር የቆመችው ማን እንድሆነች በማህፀኗ የያዘችው ማን እንደሆነ ብታውቁ ኖሮ ቀድማችሁ ያስገባችሁዋቸውን እንግዶች ሁሉ ''በህግ አምላክ ውጡልን'' ብላችሁ ማስወጣታችሁ አይቀርም ነበርና ትሰሙ እንደሆን እኔ ልንገራችሁ:: ብታውቁአት ኖሮ እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት....

''የጌታችን እናት ወደ እኛ ትመጪ ዘንድ እኛ ምን ነን?'' ተትሏት ነበር::
እናንተ የእንግዶች ማደሪያ ባለቤቶች ሆይ! እርግጥ ነው እናንተ ከበር የመለሳችሁት እንዲት የፀነሰች የገሊላ ናዝሬት እንግዳ ብቻ ነበር::

ለእርስዋ ቦታ የለም ብሎ መናገርም ቀላል ነገር መስሎአችሁ ሊሆን ይችላል::

እመኑኝ ለእርስዋ ''አንቺን ለማሳደር ቦታ የለንም'
ስትሉአት ግን ማንን እንደመለሳችሁት አላወቅችሁም:: እርግጥ ነው ቦታው በእንግዳ ተይዟል ትሉኝ ይሆናል:: ግን ደሞ ለመውለድ ለተቃረበች ወጣት ሥፍራ ቢጠፋ እንኳን የራስም አልጋ ቢሆን መልቀቅ አይገባም ነበር?
ለአንዲት ለምትወልድ እናት ቸርነት ምድረግ ሰብአዊ ግዴታ አይደለምን? ብታደርጉ ኖሮ የምታገኙትን ከጠበቃችሁት በላይ በሆነ ነበር::

እርስዋን ብታስገቧት ኖሮ የሰማይና ምድሩ ንጉስ ኢየሱስ ከቤታችሁ ይገባ ነበር:: በቤታችሁ ውስጥ ከምድር እስከሰማይ የሚደርስ መሰላል ተዘርግቶ እልፍኛችሁ በመላዕክት ዝማሬ በእረኞች ደስታ በሰብአ ሰገል ስጦታ ይጥለቀለቅ ነበር:: እናንተም ከሞታችሁ በኃላ ጭምር ለዘመናት እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ የዓለም ህዝብ እየመጣ የቤታችችሁን ወለል ይስም በደጃፋችሁም ይንከባለል ነበር::

#አቤት_ድንግል_ማርያምን '' #ቦታ_የለንም'' ብሎ ከደጅ መመለስ የሚያስከፍለው ዋጋ የሚያሳጣው ጸጋ እንዴት ያለ ነው?! ምነው እንደ እናንተ በዚያ ዘመን በኖርኩና ድንግል ማርያምን ከደጄ ቆማ አግኝቻት ከአልጋዬ ወርጄ በተቀበልኳት!

#እመኑኝ_ለማርያም_ቦታ_የለኝም_ያለ_ሰው_ቦታ_ያጣ_ለኢየሱስ_ነው::

እርሷን ወደ ቤቱ ግቢ ያላት ሰው ግን ጌታን ወደቤቱ ያስገባዋል::

#ጌታ_ያለው_ደሞ_ሁሉም_አለው::

አይ እናንተዬ! ሌላ እንግዳ ከምታግበሰብሱ ለአንዲት ድንግል ቦታብትሰጡአት ኖሮ ቤታችሁ ሰማይ ይሆን ነበር::

#የግዮን_ወንዝ

#ዲያቆን_ሄኖክ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ


#መልካም_የልደት_በዓል_ይሁንልን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →