AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ዘኪዎስ_አጭር_ባይሆን_ኖሮ
ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት::
የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::
እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም::
#ጌታ_ሊታዩ_ከሚሞክሩት_ይልቅ_ሊያዩት_የሚሹትን_ይወዳልና_ዘኪዎስን_ጠራው::
ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: 'ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል' አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::
ዘኪዮስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋርእየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::
ዘኪዎስ አጭር_ባይሆን_ከዛፍ_ላይ_አይወጣም_ነበር::
አጭር ባይሆን የሠራዊትአምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር::
በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉስ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሊያሳንሰው ነበር::
በምድር በመፅሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው::
ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ....
#እግዚአብሔር_ለነፍሳችን_መዳን_የሚያሳጥርብን_ብዙነ_ገር_አለ::
እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥር ነገር ግን አይጠፋም::
ይሔ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እነሱን ማለቴ ነው:: ይሄ ይጎድልብኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
#እጥረትህ_መክበሪያህ_ነው::
#ጉድለትህም_መዳኛህ_ነው::
እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያት ይሁንህ::
በጉድለትህ እንደዘኪዎስ ከፍ በልበት::
ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም:: ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል::
#ከዚያም_ስላጠረህ_ስለጎደለብህ_ነግር_ፈጣሪን_ስታመሰግነው_ትኖራለህ::
#እመነኝ_አንዳንድ_ጉድለቶች_እድሎች_ናቸው::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::
ግንቦት 23 2014
አዲስ አበባ
#የግዮን_ወንዝ
#ዲያቆን_ሔኖክ_ኃይሌ
ሙሉ ገቢው #ለደብረ_አሚን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ቤተ ክርስትያን የሕንፃ እድሳት ሥራ የሚውል ነውና ሁላችንም ይህን መፅሐፍ በመግዛት አሻራችንን እናሳልፍ ከመፅሐፉም እውቀትን እንሸምት እላለሁ
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ::
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2457
557