AB PHOTOGRAPHY & graphic design
#ጥበብ
የንጉስ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ከጥበቡ ጥበብ ከእምልኮው አምልኮ ልትቀስም ንግስተ አዜብ ማክዳ ጥበብን ናፈቀች::
የመንገዱን ርዝመትና አስቸጋሪነት በአግባቡ የተረዳችው ቢሆንም ለንግስት ማክዳ ከድካም በላይ ጥበብ በለጠችባት::
አማካሪዎቿም " እመቤታችን ሆይ! ጥበብ እኮ ካንቺም አልታጣም! ጥበብን አጥብቀሽ የምትወጂው በጥበብ ነው:: ጥበብ ትጠራሻለችና:: እኛ ግን አንቺ ብትሔጂ ከአንቺጋር እንሔዳለን:: ሞትም ቢሆን ሞታችን ካንቺ ጋር ይሆናል:: ሕይወትም ቢሆን ሕይወታችን ካንቺ ጋር ይሆናል " አሏት
ንግስተ ሳባ ማክዳ የንግስትነት ክብሯ ሳይከለክላት የሴትነት ጉልበቷ ሳያግዳት ጥበብን ፍለጋ ተራራ ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ ጋር ሸንተረር አልፋ ባህር ብረኃ አቋርጣ ተሻግራ ወደ ኢየሩሳሌም ረጅሙን ጉዞ ተጟዙች::
797 ግመል ቁጥሩ በማይትወቅ በቅሎዎችና አጋሰሶች ብዙ ወርቅ ብር የዝሆን ጥርስ ሽቱ የከበሩ ድንጋዮች ለስጦታ ተጭኖ ትልቅ ቅፍለት ይዘው ወደ ቀይባህር ዳርቻ ተጟዙ:: በብዙ መርከቦች ተሻግራ የዐረቢያን በረኃ አቋርጣ ኢየሩሳሌም ደረሰች::
የጥንካራዋ ሴት ልጆች ነን:: የዚች ባለ ብሩህ አእምሮ ንግስት ልጆች ከጥበብ ማዶ ሆነን ከዓለም ስልጣኔ ጭራ ሁነን መገኝታችንን ዛሬ ተነስተን ብታይ ምን ትለን ይሆን? ጥበብን ፍለጋ ሳይሆን ሳንቲም ፍለጋበዓለም ሁሉ እንደ ጨው ዘር የምንበተን ምስኪን ሕዝቦች መሆናችን ብታይ እንዴ ታዝንብን ይሆን??
የንግስት ማክዳ ልጆች ነን የጥበብ ፈላጊዋ የጥበብ አሳሿ መቼ ይሆን ወደ ጥንት ክብራችን እንመለስ ብለን ሆ ብለን የምንነሳው የሞራልና የደግነት የአብሮነት የታታሪነት የጀግንነት የነፃነት ልዕልና የአልፋ ኦሜጋ ጥበብ ባለቤት ለመሆን በቁጭት የምንነሳው?!
ንግሥተ አዜብ ማክዳ ኢየሩሳሌም እንደደረሰች ንጉስ ሰሎሞን በክብር ተቅበላት:: ጥበቡን ሁሉ አካፈላት:: ያቀረበችለትን እንቆቅልሾች ሁሉ ፈትቶ ጥበበኝነቱን አረጋገጠላት:: የአባቶቹን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ሥርዓተ አምልኮና የታቦተ ጽዮንን ቃልኪዳን ሁሉ አስረዳት::
የቤተ መንግስቱን ባለሟሎች ስንዱነት ሁሉን አነሳያት:: ለጉብኝቷ ማስታወሻ ለሀገሯ ስም መጠሪያ ይሆን ዘንድ በኢየሩሳሌምና ባቅራቢያዋ ርዕስት ጉልላት ሰጣት:: ለውበቷ ለንፅህናዋ ልብሩህ አዕምሮዋ አድናቆት ልብ አልቀረለትም ነበርና በፍቅሯ ወደቀ::
ከማህፀኗ ዘር ያስቀር ዘንድ ተጋ:: እናም ሆነ! እርሱም ለእርሷም በኩር የሚሆነውን ልጁን ከሀገሯ ተመልሳ ቀዳማዊ ምኒልክን (እብነ ሀኪም) ውለድች::
ክጉዞዋ መልስም የተመኘችውን ጥበብ የሰሎሞንን ማስተዋን በጥልቅ እንደቀሰመች ተናገረች::
"ወድ ጥበብ በር ዘልቄ ገባሁ:: ወድ ጥልቁ መረዳት ሰመጥሁ:: ወደ ዕውቀት ጮራ አቀናሁ በእኔምልይ ጥበብ ብርሃኗን አበራች:: ጥበብን ጋሻ አደረኳት በራስ መተማመኔ ጠበቅሁ::ደግሞም ለእኔ ብቻ አይደለም ጥበብን ፍለጋ ለተጟዙ ሁሉ ለሀገሬ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ሁሉ እንጅ::"
ድግሞም አለች:
" ከእንግዲህ ወገኖቼ! እውነትን ውደዱ ሐሰትን ጥሉ:: አዎን! ሽፍጥን ጭቆናን በእናንተ ዘንድ አስወግዱ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነውና እናንተም በአንድ አምላክ ሥር ቤተሰብ ሆናችኃልና!"
ቀዳማዊ ምንትልክም በጥበብና በሞገ አደገ:: እናቱ ንግስት ማክዳ አባቱን እንዲጎበኝ ወደ ኢየረሳሌም ላከችው:: በጉብኝቱም በአባቱ በንጉስ ሰሎሞን ፊት ሞገስን አገኘ:: አባቱ በእጅጉ ወደደው:: በመንበሩ ሊላስቀምጠው በመንግስቱ ሊሰይመው በልቡ ፈቀደ:: ይህንንም ነገር አለው:-
"እግዚእብሔር ከወደድ እስከ እባቴ ዕድሜ ድረስ ያድርሰኝ:: ወደ አብባቴና አባቶቼ ከተወሰድኩ እንተ በዙፋኔ ላይ ትቅመጣለህ:: በእኔ ፋንታም ትነግሳለህ:: የእስራኤል ሊቃውንት ፍሞ ይወዱሃል:: እኔን ድድካማው በአባቶቼ ዙፋን ታየኛለህ:: ከእኔም በኃላ አንተ እንደኔ ትሆናለህ::"
አባቱ ጥበበኛው ንጉስ ስሎሞን በእስራኤል ሀገር ከእርሱ ዝንድ ቢቀር መንግስትን እንድሚያወርሰው ዙፋኑን እንድሚሰጠው ነገረው:: የከበረችውን ታቦተ ጽዮን መማፀኛው ትህነ ዘንድ ባቅራብያዋ እንድእሚሆን ጥበቡንና ሁብቱን ሁሉ እንደሚሰጠው ቃል ግባለት:: እንደወጣትነቱም ውብ ልዕልት ወዕቁባት እንድሚድርለት ነግሮ አባበለው::
ቀዳማዊ ምንልክ ግን ክዚህ ሁሉ ሥልጣንና ተድል ይልቅ እናቱንና የእናቱን ሀገር ኢትዮጵያ በለጡበት::
እናም:- "ጌታዬ አባቴሆ! እናቴንና ሀገሬን እተው ዘንድ አይቻለኝም:: እናቴ በቶሎ ወደ እርሷ እንድመለስ እንጂ እዚህ እንዳልቀር በጡቶቿ አምላኛለች የእስራኤል አምላክ ታቦትም ባለሁበት ትባርከኝ:: ፊትህን ላይ ቃልህን ልስማ በረከትህንም ልቅበል ወድ እናቴም በድህና እሔድ ዘንድ ሽቻለሁና ጸሎትህ በሄድኩበት ትከተለኝ" አለው ቁርጥ አድርጎ::
ሃይማኖትህን ያለ ሀገር ሆነህ የትም ልታከብረው ትችል ይሆናል ሀገር ስታጣ ግን ሁሉ ታጣለህ:: ኦርቶዶክስን ግብፅ እስልምናን መካ መዲና ካቶሊክን ቫቲካን ፕሮቴስታንትን ጀርመን ታገኝ ይሆናል:: #ኢትዮጵያ_ግን_የትም_የለችም:: #ሃይማኖታችን_የምኖደው_ኢትዮጵያን_ቀድሶ_ስለሰጠን_ነው #ኢትዮጵያን_የምንወዳት_ሃይማኖታችንን_እጅግ_መንፈሳዊና_ከፈጣሪ_ጋር_የሚያገናኘን_ንጹህ_መንገድ_ስላደረገችልን_ነው::
<እኛም የንግስት ማክዳ ልጆች ነን የጥበብ ፈላጊዋ የጥበብ አሳሿ አኦን የቀዳማዊ ምኒል ልጆች ነን እናት ሀገራችንን ፍፁም ወዳጅ ሥልጣን ምቾት የማይለውጠን ታማኝ!> ለማለት መቼ ይሆን የምንደፍረው!
የልጁን ቁርጥ ቃል የሰማው ንጉ ሰሎሞን ልቡ ታወከ:: ልቡ የወደደውን የበኩር ልጁ በእርሱ ዝእንድ እንደማይቆይ ተረዳ:: እናም መንገዱን ሊያሰናክልበት አልፈቀድም:: ሹማምቱና ሽማግሌዎቹን በየነገዳቸው ጠርቶ:
"የአብራኬ ክፋይ የበኩር ልጄ ተመልሶ ወደእናቱና ሀገሩ ሊሔሄድ ነው:: እናም ብቻውን ይሔድ ዝንድ አይገባምና የእስራኤል በኩር ሁሉ አብሮት ይሂድ!" አለ::
<ክብረ ነገስት> የተባለው ጥንታዊ መጽሐፍ እንድሚተርክልን በዚህ ውሳኔ መሠረት ቀዳማዊ ምኒልክ በብዙ እስራኤላውያን በኩራት ታጅቦ ታቦት ጽዮንን በስጢር ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ::
#ሚተራሊዮን
#ዓለማየሁ_ዋሴ_እሸቴ
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ
ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD