AB PHOTOGRAPHY
@abiy_yemaryam_lej"ነፃ ጥሪ እና ቀላል የሆኑ ቁጥሮች የአደጋ የጊዜ ስልክ መስመሮች ናቸው፡፡ እነዚህን ቁጥሮች ከአደጋ ቀን ውጪ ማንም አይፈልጋቸውም ፡፡ጸሎትን ችግር ሲኖር ብቻ የምንጠቀው በሰላም ቀን ግን የምንረሳው መስመር አይደለም፡፡ ጸሎት አባት ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ የፍቅር ግንኙነት ነው እንደመልካም ልጅ አባታችን ሲናፍቀን የምናደርገው እንጂ ልማዳዊ ስርአት አይደለም፡፡ ፀሎት የናፍቆታችን እርካታ ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ጸሎት እውቀት ስለሚመስላቸው እኔ ጸሎት አላቅም አልችልም ይላሉ፡፡ እነዚት ሰዎች አባቴን ለማናገር ኮሌጅ ገብቼ መማር አለብኘ እንደሚል ጅል ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ ለፀሎት የሚያስፈልገው ፍቅር ብቻ ነው፡፡
የቀደሙት አባቶች የፀሎትን ሚስጥር ሲናገሩ.....
"ጸሎትስ ይእቲ ተናግሮተ ሰብእ ኀበ እግዚአብሔር ልዑል"
"ፀሎት ማለት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ነገር ናት"
ሁላችንም በሀይማኖታችን ስለሀገራችን ስለአለም እንፀልይ😔🙏🙏
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን
#street_photography
#best #awesome #timing
#photoshoot
#our #lovely😍 #Ethiopia