TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #2391 · Back to latest

Older Posts 11 shown
Post #2390 579
AB PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryam_lej

#እንኳን_ለፃድቁ_አቡነጎርጎሪዮስ_ዘላዕላይ_ግብፅ_በዓለዕረፍት_አደረሳችሁ

#ቦሌ_ሚካዔል_አቡነጎርጎሪዮስ

#street_photography


#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Post #2389 538
AB PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryam_lej

#እንኳን_ለፃድቁ_አቡነጎርጎሪዮስ_ዘላዕላይ_ግብፅ_በዓለዕረፍት_አደረሳችሁ

#ቦሌ_ሚካዔል_አቡነጎርጎሪዮስ

#street_photography


#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #Ethiopia
Post #2384 811
የድንግል ማርያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን

አንድሽ ጎበዝ ተማሪ ነው ለትምህርት ዋጋ ከፍሎላታል በእርግጥ እዚአብሔር ይመስገን እሷም በግድም ቢሆን ውለታውን መልሳለታለች!::

ጎበዝ ተማሪ ስለነበር 12ኛ ክፍልን እንደጨረሰ ዩንቨርስቲ ግብቶ ማጥናት የሚፈልገው ህክምና ነበር::

ግን እግዚአብሔር አልፈቀደም በጣም ጎበዙ ተማሪ ያልጠበቀው ክስተት ተከሰተ አስተማሪዎች ጎደኞቹ ቤተሰቦቹን ሁላችንንም ያስደነገጠ ያሳዘነ ገጠመኝ ...🤦‍♂️🥺🥺🥺

አንድሽ ማትሪክን ወደቀ.....😔😔🥺🥺🥺

ሁላችንም ማመን ነበር ያቃተን አአቀስን አዘንን::

አንድሽ ከትምህርት ቤት ውጤቱን ሰምቶ በጣም ተረብሾ ነበር እያለቀሰም ነበር ግን ቀጥታ የሔደው ወደሌላ ቦታ አልነበረም ወደቤተክርስቲያን እንጂ...
የት ቤተክርስቲያን? ባዕታ ማርያም ያለችው ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እዛ ሔዶ አለቀሰ ችግሩንለሷ አዋያት እያለቀስ ተማፀናት ማን እንደሆንኩ ካልተማርኩኝ ምንም ተስፋ እንደሌለኝ አንቺ ታውቂያለሽ ሌላ ዘመድ ጟደኛ የለኝ እያለ ሁሉንም ነገራት..........

በተቻለው መጠን ቤተሰብ እንዳይረበሽ ራሱን ለማረጋጋት ሞከረ....ካጠገቡ ላፍታም አልተለየሁም ነበር ውሎአችን ቤተክርስቲያን ሆነ ረጅም የእግር መንገዶችን እንረግ ነበር......ከቀን ወደ ቀን እየተረጋጋ እየተረጋጋ መጣ ሁሉም ነገር ለበጎ እንደ እንደሆነም አመነ::

አንድሽ በፈጣሪ ላይ ያለው እምነት በጣም ያስድንቀኛል::.........

ከዛም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማታው መርሃግብር ለመማር ይወስናል........ምን እንደሚማር ስናጠያይቅ ቆይተን የሰው ወሬ ግራ ሲያጋባን አሁንም ወደ ኪዳነ ምህረት ቤተክርሲቲያን ሔዶያሉትን ኮርሶች በወረቀት ላይ ፅፎ ድንግል ሆይ አንቺ ታውቂያለሽ ብሎ አንዱን መረጠ የደረሰውም ሲቪል ኢንጂነሪንግ ነበር::

ምንም አላንገራገረም እሱን መረጠ......አዲሳባ ዩኒቨርስቲ ገባ.......

ህይወት አንዴ በመውደቅ ብቻ አትቆምም....

ኢንጂነሪንጉን እያጠና ሁለተኛ አመት ላይ በሀገራችን ግዙፉ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም በቀን መርሃ ግብር ለመማር ፈተናውን ወሰደ በጥሩ ውጤት አጠናቆ....በሆቴል ማኔጅመንት መማር ቀጠለ የሆቴል ስራ እንደ አንድሽ ላለ መልካም ሰው ትክክለኛ ሙያ ነው::

እዛም ሶስት አመቱን ተምሮ...በጥሩ ብቃት አጠናቆ ከኢንጂነሪንጉ ቀድሞ በማኔጅመንት ተመርቆ ስራ ገባ በእንድ ትልቅ በሚባል ባርና ሬስቱራንት ሱፐርቫይዘር ሆኖ ተቀጠረ በስራው የተመሰከረለት ነበር......

እዛ እየሰራ በሀገራችን ግዙፉ የሆነው ሆቴል ተከፈተና እዛ ተወዳደረ.....ሁሉን በብቃት አልፎ ትልቁ ሆቴል ላይ ስራ ጀመረ.....ጥሩ ተከፋይ ሆነ

እግዚአብሄር አምላክ አንኳኩ ይከፈትላችኃል አለ እንጂ በሩ ጋር ቁሙ ይከፈታል አላለም...መጣር ያስፈልጋል........

እዛም እየሰራ ኢንጂነርጉንም እያጠናከር ተምሮ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኝ::
.
.
.
አንድሽ አልኩት....እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ዲግሪህን ይዘኃል ቀጣይ እሱ ከፈቀደ ወደ ትዳር ነው ትዳር ላይ ከገባህ ለመማር ይቸግርህ ይሆናል ስለዚህ ማስተርስህን መማር አለብህ አልኩት...በሀሳቡ ተስማማንበት......አድማስ ዩንቨርስቲ ማስተርሱን ጀመረ........

እግዚአብሔርአምላክ ሁሌም ከቅን ሰዎች ጋር ነው አይኖቹን ለአፍታም ቢሆን ከነሱ ላይ አያነሳም....


ሁሉም አለፈ ዛሬ ውዱ ወንድሜ የማስተርስ ዲግሪውን ከአድማስ ዩኒቨርስቲ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝቷል::

ዶክትሬቱም ይቀጥላል.......

እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዝጋ ምእራፉ
እግዚአብሔር ሊያሸንፍ የሱ ሆኖ ሰልፉ
መልካም ለመናገር አፉ ባይታደል
ይህን እስኪያይ ጠላት ምናለ ዝም ቢል

መልካሙን ድብቆ ክፉን እያሳየ
ይለኝ ነበር ጠላት እግዚአብሔር ዘገየ
ግን ሁሉን በጊዜ ውብ አርጎ ሲሰራ
አፍሯል ለዘላለም ድንቆት የሱ ስራ


ታዲያ ይሔን ታሪክ አንብበህ ተስፋ ስለመቁረጥ ታስባለህ??? አሁንያለህበት አንተን አይመጥንህም ከዚህ ከፍ ማለት አለብህ....ላንተ የሚገባህ የተሻለ ነገር ነው ዝም ብለህ ተማር ቢያንስ አለቃህን ትቀንሳለህ.......

እግዚአብሔር መልካም ሰዎችን ጣለ ተብሎ የቱም ጋር አልተፃፈም......አንዱ ማሳያም አንድሽ ነው...እንኳን ደስ አአህ የድንግል ማርያም ልጅ ይጠብቅህ.....የምቶዳት እናትህ እመብርህን ወላዲተ አምላክ በመንገድህ ሁሉ እሷ ትቅደም::

ቀጣይ አጎት መሆን እፈልጋለሁ...🤪🤣😁

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ::
Post #2380 821
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን ከዘመን ማርቆስ ወደዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና አሸጋገርዎት። 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌼ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እንደዚህ ይላል:-

"ክርስቲያን ነህን??

ወዳጄ ሆይ ክርስቲያን ነህን?? እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላላስፈለግ ግብር አታውለው::

እጅ የሰጠህ እንድትሰርቅበት ሳይሆን ትዕዛዛቱን እንድትፈፅምበት በጎ ምግባር እንድትሰራበት ለፀሎት እንድትነሳበት የወደቁትን እንድትናሰበት ነው::
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ጆሮን የሰጠህ ተራ ወር እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታደምጥበት ነው::

አንደበትን የሰጠህ እንድትስድበትና እንድትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት እንድታመሰግንበት እንድትመሰክርበት ነው::

እግርን የሰጠህ ወደክፋት ሳይሆን ወድበጎ ስራ እንድትፋጠንበት ነው::

ሆድን የሰጠህ ለመብል ብቻ ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው::

ፈቲውን የሰጠህ እንድታመነዝርበትና እንድትዳረበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው::

ገንዘብና ጉልበትን የሚሰጠህ ሰማያዊ ቤታችንን እንድንሰራበት ነው::

🌼🌼💐🌻💐🌹🌹🌹🌷🌼

እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት::

እግዚአብሔርን ትጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመስግነው::

የማይረባንንነገር ለምነነው ፀሎታችንን ከሚሰማን ባይሰማን ይሻለናል::

•"መፅሐፍ እንዳለእናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠትን ካወቃችሁ ከእናንተ በላይ የስጦታን ምንነት መቼ መስጠጥ እንደሚገባን ምን መስጠትም እንዳለበት የሚያውቅ እግዚአብሔርም መስጠት ያውቅበታል"

ለዚህም ነው ብፁዕ ጻውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ ፀሎቱን ያልሰማው:: ለዚህም ነው የተወደደ ሙሴ ፊትህን አሳየኝ ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው::

ስለዚህም እኛም ፀሎታችን ባይሰማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ::


ፀሎታችን ባይሰማ ግን አምላክ የሚያደርገው ሁሉም ለጥቅማችን ነውናበፍፁም አንዘን::

አምስቱ የንሰሃ መንገዶች እና ሌሎች
በቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ

ትርጉም ገብረእግዚአብሔር ኪደ

ሩጫችን መሆን ያለበት ከትላንት የተሻልን ለመሆን ነው የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጥን::

ለውጡ የቀን የአመት ብቻ እንዳይሆንብን እንጠንቀቅ በተቻለን መጠን መልካምነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፍል እንዘጋጅ ጥሩ እንሁን ከባዱ ሰውን መውደድ ነው ሰውን መጥላት የመጨርሻ ቀላሉ ነገር ነው::


መልካም አዲስ አመት አብይ የማርያም ልጅ ነኝ::

🌻🌻💐💐💐🌼🌼🌼💐💐🌹🌷🌹🌷
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →