AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
አሁን ነው እርቦኛል ብሎኝ ቁርስ አብልቼ ትንሽ ተጫወት ብዬው ነው::
አብዬ አብዬ አብዬ አለኝ እዝን ባለ ድምፅ እየሮጠ ወደኔ እየመጣ....
ምንድነው አልኩት ንባቤን አቁሜ
እዝን ብሏል አይኖቹ እንባ አቅረዋል...🥺🥺
ምንድነው ምን ሆነህ ነው.......??
መታኝ.....
ማ.......
ያኛው....ልጅ...
እንዴ ታዲያ አንተም አትመታውም ነበር እንዴ ይሔ ያቅትሃል አልኩት
እሱም እንዲ አለኝ....
እሱ እኮ አባት አለው አለኝ.......🥺😢🥺
ንግግሩ ሁኔታዎቹ ሀዘኔታው ምን ያህል እንደከፋው ሁልጊዜም ቢሆን ካይኔ አይጠፋም......ውስጥ ድረስ ዘልቆ ተሰምቶኛል......አቀፍኩት እንባዬም ሳላስበው ጠብጠብ አለ........
አቅፌው እንዲህ አልኩት ታዲያ ይኑረዋ እንዴ እኔስ ያንተ አባት አይደለሁ እንዴ ማንንም እንዳትፈራ እሺ እኔ አለሁልህ እሺ.....ንግግሬን ሳግ አፍኖት ነበር
እውነት አለኝ
አው በእውነት እኔ አለሁልህ እሺ........ብዬ እቅፍ አድርጌ ሳምኩት....
የተደሰተው ደስታ ልነግራቹ አልችልም ወድያው ለጟደኞቹ ሊናገር ወጣ.....
ይኽው ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን መንገድ ላይ ቤተክስቲያን ትምህርት ቤት የትም ይየኝ አባዬ አባዬ እያለ ነው የሚጠራኝ......🥺🥺🥺
እናታቸው ባሏ ጥሏት ሔዶ ቡና እያዞረች ብቻዋን የምታሳድጋቸው ሁለት ምስኪን ልጆች አንዱ ነው እንዲ ያለኝ.......እናታቸው ከስራ እስክትመጣ እኔጋር ነበር የሚቆዩት..........
እናታቸውም እናቱ እንደዚ ትለዋለች
"አንተ ልጅ አባቴ አባቴ እያልክ ልጁን ሚስት እንዳታሳጣው"
ፈገግታ ይከተላል.......😁😁😁ሳቃችን ምን ማይደብቀው ነገር አለ.......
አብይ ይማርያም ልጅ ነኝ........
አስተያየታችሁን አድርሱኝ
@jahABP ነኝ