TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2384 811
የድንግል ማርያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን

አንድሽ ጎበዝ ተማሪ ነው ለትምህርት ዋጋ ከፍሎላታል በእርግጥ እዚአብሔር ይመስገን እሷም በግድም ቢሆን ውለታውን መልሳለታለች!::

ጎበዝ ተማሪ ስለነበር 12ኛ ክፍልን እንደጨረሰ ዩንቨርስቲ ግብቶ ማጥናት የሚፈልገው ህክምና ነበር::

ግን እግዚአብሔር አልፈቀደም በጣም ጎበዙ ተማሪ ያልጠበቀው ክስተት ተከሰተ አስተማሪዎች ጎደኞቹ ቤተሰቦቹን ሁላችንንም ያስደነገጠ ያሳዘነ ገጠመኝ ...🤦‍♂️🥺🥺🥺

አንድሽ ማትሪክን ወደቀ.....😔😔🥺🥺🥺

ሁላችንም ማመን ነበር ያቃተን አአቀስን አዘንን::

አንድሽ ከትምህርት ቤት ውጤቱን ሰምቶ በጣም ተረብሾ ነበር እያለቀሰም ነበር ግን ቀጥታ የሔደው ወደሌላ ቦታ አልነበረም ወደቤተክርስቲያን እንጂ...
የት ቤተክርስቲያን? ባዕታ ማርያም ያለችው ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እዛ ሔዶ አለቀሰ ችግሩንለሷ አዋያት እያለቀስ ተማፀናት ማን እንደሆንኩ ካልተማርኩኝ ምንም ተስፋ እንደሌለኝ አንቺ ታውቂያለሽ ሌላ ዘመድ ጟደኛ የለኝ እያለ ሁሉንም ነገራት..........

በተቻለው መጠን ቤተሰብ እንዳይረበሽ ራሱን ለማረጋጋት ሞከረ....ካጠገቡ ላፍታም አልተለየሁም ነበር ውሎአችን ቤተክርስቲያን ሆነ ረጅም የእግር መንገዶችን እንረግ ነበር......ከቀን ወደ ቀን እየተረጋጋ እየተረጋጋ መጣ ሁሉም ነገር ለበጎ እንደ እንደሆነም አመነ::

አንድሽ በፈጣሪ ላይ ያለው እምነት በጣም ያስድንቀኛል::.........

ከዛም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማታው መርሃግብር ለመማር ይወስናል........ምን እንደሚማር ስናጠያይቅ ቆይተን የሰው ወሬ ግራ ሲያጋባን አሁንም ወደ ኪዳነ ምህረት ቤተክርሲቲያን ሔዶያሉትን ኮርሶች በወረቀት ላይ ፅፎ ድንግል ሆይ አንቺ ታውቂያለሽ ብሎ አንዱን መረጠ የደረሰውም ሲቪል ኢንጂነሪንግ ነበር::

ምንም አላንገራገረም እሱን መረጠ......አዲሳባ ዩኒቨርስቲ ገባ.......

ህይወት አንዴ በመውደቅ ብቻ አትቆምም....

ኢንጂነሪንጉን እያጠና ሁለተኛ አመት ላይ በሀገራችን ግዙፉ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም በቀን መርሃ ግብር ለመማር ፈተናውን ወሰደ በጥሩ ውጤት አጠናቆ....በሆቴል ማኔጅመንት መማር ቀጠለ የሆቴል ስራ እንደ አንድሽ ላለ መልካም ሰው ትክክለኛ ሙያ ነው::

እዛም ሶስት አመቱን ተምሮ...በጥሩ ብቃት አጠናቆ ከኢንጂነሪንጉ ቀድሞ በማኔጅመንት ተመርቆ ስራ ገባ በእንድ ትልቅ በሚባል ባርና ሬስቱራንት ሱፐርቫይዘር ሆኖ ተቀጠረ በስራው የተመሰከረለት ነበር......

እዛ እየሰራ በሀገራችን ግዙፉ የሆነው ሆቴል ተከፈተና እዛ ተወዳደረ.....ሁሉን በብቃት አልፎ ትልቁ ሆቴል ላይ ስራ ጀመረ.....ጥሩ ተከፋይ ሆነ

እግዚአብሄር አምላክ አንኳኩ ይከፈትላችኃል አለ እንጂ በሩ ጋር ቁሙ ይከፈታል አላለም...መጣር ያስፈልጋል........

እዛም እየሰራ ኢንጂነርጉንም እያጠናከር ተምሮ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኝ::
.
.
.
አንድሽ አልኩት....እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ዲግሪህን ይዘኃል ቀጣይ እሱ ከፈቀደ ወደ ትዳር ነው ትዳር ላይ ከገባህ ለመማር ይቸግርህ ይሆናል ስለዚህ ማስተርስህን መማር አለብህ አልኩት...በሀሳቡ ተስማማንበት......አድማስ ዩንቨርስቲ ማስተርሱን ጀመረ........

እግዚአብሔርአምላክ ሁሌም ከቅን ሰዎች ጋር ነው አይኖቹን ለአፍታም ቢሆን ከነሱ ላይ አያነሳም....


ሁሉም አለፈ ዛሬ ውዱ ወንድሜ የማስተርስ ዲግሪውን ከአድማስ ዩኒቨርስቲ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝቷል::

ዶክትሬቱም ይቀጥላል.......

እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዝጋ ምእራፉ
እግዚአብሔር ሊያሸንፍ የሱ ሆኖ ሰልፉ
መልካም ለመናገር አፉ ባይታደል
ይህን እስኪያይ ጠላት ምናለ ዝም ቢል

መልካሙን ድብቆ ክፉን እያሳየ
ይለኝ ነበር ጠላት እግዚአብሔር ዘገየ
ግን ሁሉን በጊዜ ውብ አርጎ ሲሰራ
አፍሯል ለዘላለም ድንቆት የሱ ስራ


ታዲያ ይሔን ታሪክ አንብበህ ተስፋ ስለመቁረጥ ታስባለህ??? አሁንያለህበት አንተን አይመጥንህም ከዚህ ከፍ ማለት አለብህ....ላንተ የሚገባህ የተሻለ ነገር ነው ዝም ብለህ ተማር ቢያንስ አለቃህን ትቀንሳለህ.......

እግዚአብሔር መልካም ሰዎችን ጣለ ተብሎ የቱም ጋር አልተፃፈም......አንዱ ማሳያም አንድሽ ነው...እንኳን ደስ አአህ የድንግል ማርያም ልጅ ይጠብቅህ.....የምቶዳት እናትህ እመብርህን ወላዲተ አምላክ በመንገድህ ሁሉ እሷ ትቅደም::

ቀጣይ አጎት መሆን እፈልጋለሁ...🤪🤣😁

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ::
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →