AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
አንዳንድ ቀን አለ የእግዚአብሔር ክብሩ የሚታይህ ቀን አንዳድ ቀን አለ በወንጌል መካከል የምትሰምጥበት ቀን የአብን ድምፅ ባትሰማ የቅዳሴ ድምፅ የምትሰማበት ቀን አለ::
ከዚያ ደስታ ከዚያ ተመስጦከዚያ ሰላም ውስጥ ከገባህ መውጣት አትፈልግም:: ምናለ እዚያው ብቀር ምናለ አሁንየሚሰማኝ ሰላም ሁልጊዜ ቢሰማኝ ትላለህ...::
የጌታ ፊት ከፀሐይ አብርቶ ይታይህና ሌላ ፀሐይ መሞቅ ያስጠላሃል:: በሙሴ ሕግጋት ውስጥ እየተመላለስህ የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ልብህን ይሰውረዋል እንደኤልያስ ያሉትን መናኞች ቅዱሳንን ታሪክ እያነበብህ ልብህ ይመንናል::
ማቋረጥ የማትፈልገው የነፍስ እርካታን ታገኛለህ::
ሰማያዊ ሕልም እያየህ ነውና እንዳትነቃ ትሰጋለህ::
#ከዚያ_ተራራ_ከዚያ_ከፍታ_መውረድ_ያስፈራሃል::
ስለዚህ ጌታን ትማጸናለህ::
#ጌታ_ሆይ_በዚህ_መሆን_ለእኔ_መልካም_ነው::
#እባክህ_አልውረድ ትለዋለህ
ከዚህ ተራራ ከወረድኩ ምን እንደምሆን ምን እንድምሰራ አውቀዋለሁና ጌታ ሆይ እባክህ እዚሁ ብቀር ይሻለኛል:: ወርጄ ሶስቴ ከምክድህ እዚህ ሶስት ዳስ ሰርቼ አንተን ባገለግል እመርጣለሁ:: ወርጄ አላውቅህም ከምልህ እዚሁ ፊትህን እያየሁ ልቆይ!
እባክህ ከዚህ ከፍታ አልውረድ::
#ይህ_ነው_የጴጥሮስ_ልመና
ቅዱስ ጴጥሮስ መቆየት እየፈለገ ከዚያ ተራራ ሲወርድ ምን ይሰማው እንደሆን አላውቅም:: ግን እናቶቻችን ከገዳም ቆይተው ሲመለሱ የሚዘምሩት መዝሙር ሃሳብ ሳይጋራው አይቀርም:-
ነፍሴን ሀገሯን አሳየኃት
ነፍሴን ሀገሯን አሳየኃት
ከተማ ገብቼ ካላበላሸኃት!!!!!!!
ዲያቆን ሔኖክ ሃይሌ እንደፃፈው
Post #2398
821
