TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2396 658
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

በአካባቢዬ ካሉት ነገሮች ጋር ተላምጄ መኖርን እየተለማመድኩ ያለው ሰው ነኝ መለማመድ ብቻ ሳይሆን እየሆንኩም ይመስለኛል......ሰዎች ከሚከፉብኝ የነሱን ነገር ተቀብሎ ለመውደድ መሞከር.......ከዛ እኔንም እነሱንም ደስተኛ መሆን.


ከኔ ደስታ የነሱ ደስታ ይበልጣል......በነሱ ደስታ ውስጥ ደሞ የኔን ደስታ ማግኘት.....


በምሳሌ ላስረዳ.......


በስራ ቦታዬ ላይ....ሰራተኞቼ የሚያዩት አንድ ቻናል አለ በDstv የሚተላለፍ zealem የሚባል የውጪ ፊልሞችን..በአማርኛ ተርጉሞ የሚያሳይ ቻናል ስራ እንዳያስፈታ ሁሳባቸውን እንዳይሰርቅ ብዙ ጊዜ እንዳይታይ አግዳለሁ......ወጣ ስል ግን እነሱ ግን ማየት አያቆሙም::

እነሱ በጣም ነው የሚወዱት ያስቃቸዋል ያዝናናቸዋል እንዳልኳቹ ደሞ የሰው ደስታ የሚያስደስተኝ ሰው ነኝ ያንን ደስታ መቀማት አልፈልግም እና ስራ በማይኖር ሰዓት ያንን እንዲያዩ መፍቀድ ጀመርኩ.....እናም ከዛ ውስጥ ጥሩውን ነገር ለመውሰድ መሞከር ጀመርኩ.....


እናም አንድ ቀን ማታ ላይ የሆነ ፊልም እየታየ ነው...ማሽን ውሃ እየሞላሁ የሚሉትን መስማት ጀመርኩ....የህንድ ተከታታይ ድራማ ነው........


የአንድ ሴት ልጅ ድምፅ ይሰማኛል.....የሆነ ታዋቂ ሰው ቀጥሯት እሱን እየጠበቀች ነበር...


ምኖ ሆኖ ነው እዚሁ ቦታ ነው የተቀጣጠር ነው እስካሁን አልመጣም ይኽው አንድ ሰዓት ሆነኝ አልመጣም....ስንት ስራ ጥዬ እንደመጣሁ ያውቃል ነግሬዋለሁ......ትላለች ቆንጅዬዋ ልጅ መነፅሯ አንዳች ውበት አላብሷታል ፀጉሯ የክረምት ወራጅ ውሃ ይመሰለ ረጅጅጅጅምምም ነው ወዲና ወዲ ስትመላለስ ንፋሱ ብትን ሲያደርገው ያን ቆንጆ ፊቷን ይሸፍነዋል በነዛ እንደወታደር ስለፍ ቀጥ ባሉ ድንቅ ሰዓሊ የሳላቸው በሚመስሉ ንቅሳቶች የተንቆጠቆጡት ጣቶቿን ብድግ አድርጋ ከፈቷ ላይ አንስታ በጆሮዎቿ ላይ ትሽጣቸዋለች......


አሁንም አልመጣም ሁለት ሰዓት ሆኗታል ምርር ብሏት እየተበሳጨች ባለችበት ሰዓት ካሜራው ወደ አንድ መኪና ጋር ይወስደናል.....

በመኪና ውስጥ ያ የቀጠራት ታዋቂ ዘፋኝ አለ እሰይ ሰራሁላት 2ሰዓት መሉ አስጠበኳት ሃሃሃ😂😂😂 የታባቷ....አሁን ይበቃታ.....ብሎ የሸሚዙን ኮሌታ ቀጥ አድርጎ ማርያም ጣቱን ከምላሱ ጋር አገናኝቶ ቅንድቦቹን አስተካክሎ ከመኪና ወረድ እንደወረደ ሸሚዝ ውስጥ ሱሪውን ከተተ ፀጉሩን አስተካከለ....

ካሜራችን ወደ ልጅቷ ይመልሰናል...እንዲያ ተናዳ ልትሔድ ባለችበት ሰዓት ድንገት እሱ ከመኪናው ሲወርድ ታየዋለች........

በጣም ትናደዳለች....

አውቆ ነው እያየኝ ነበር ማለት ነው ይሔን ሁሉ ሰዓት ያስቆመኝ እያላገጠብኝ ነበር ማለት ነው...😡😡😡ለምን? ስራዬን ትቼ እንደመጣሁ እያወቀ..??

ወደሷ መምጣቱን ስታይ እንደተናደድኩማ ማወቅ የለበትም........ምንም ማወቅ የለበትም አለች...


እሱም በኩራትወደሷ መጣ ሃሃ እ አስጠበኩሽ አ ሃሃ ይሄ ሁሉ ሰዓት ትግስት ኖሮሽ ትጠብቂኛለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበር......ሰራሁልሽ 2 ሰዓት ሙሉ አስቆምኩሽ አላት....

እሷም እንዲ በጥበብ እና ብልጠት በተሞላበት ንግግር እንዲ አለችው..........

አውቀህ እያየኽኝ ነበር ማለት ነው አይደል?? የኔስ ይሁን አክብሬህ ነው ስራውን ለማግኘት ነው ግን አንድ የተከበረ ታዋቂ ዘፋኝ ለአንዲት ለማትረባ ልጅ ብሎ ሁለት ሰዓት መሉ ስራ መፍታቱ በጣም ይገርማል ስራዬ አድርገኸኛል ማለት ነው ያን ያህል ቦታ ሰጥተኸኝ ነው የምትከታተለኝ ማለት ነው?? በጣም የሚያስደስት ነገር ነው.....ያን ያህል ታደርጋለህ ብዬ ጠብቄ አላውቅም ነበር ለማንኛውም ስራ መግባት አለብኝ ልሒድ...ከዚህም በኃላ ወደኔ ለመቅረብ የምታደርጋቸው ማንኛውም እንቅስቃሴዎች ምን ያህል ቦታ እንደሰጠኸኝ ነው የሚያሳዩኝ.....ቀጥልበት እንዴት ደስ ይላል......ብላው ባለበት ጥላውሔደች::

እሱም ባለበት ደርቆ ቆሞ ቀረ.....

እሰይ እንዳቃጠለኝ ሰራሁለት የታባቱ...እያለች እየሳቀች ካጠገብ ጠፋች...

እኛም ሰዎች አውቀው ሆን ብለው እኛን ለመጉዳት ከሚያደርጉት ነገር ውስጥ መልካሙን ነው ማውጣት ያለብን ያ ነው የሚያናዳቸው ክፋትን መመለስማ ለነሱ ምርቃት ነው....ይህን ተምሬበታለሁ::

መልካሙን አጉልቶ ክፉውን አሳንሶ የሚያይ ልብ ይስጠን.....

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ መልካም ጊዜ ተመኝሁ::
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →