TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59745 5.53K
ሠራዊቱ የአርሶ አደሮችን ሰብል የማረም ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም
 
በደቡብ ዕዝ ተወርዋሪው ኮከብ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና የሚገኙ አርሶ አደሮችን ሰብል በማረም ድጋፍ አድርጓል።

የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ ሻለቃ ግርማ አሰፋ እንደገለጹት፣ ክፍለ ጦሩ ከግዳጅ ተልዕኮው ጎን ለጎን በሚሰማራባቸው አካባቢዎች ለህዝቡ የተለያዩ የድጋፍና የልማት ሥራዎችን ያከናውናል።

አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖችን በገንዘብና በጉልበት መደገፍ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል መሆኑን የገለጹት ሻለቃ ግርማ፣ ይህም "ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር" የሚለውን የተቋሙን እሴት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት ሃምሳ አለቃ የሂኔስ አብራሌ እና ሃምሳ አለቃ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው፣ ከግዳጃቸው ጎን ለጎን ህዝቡን ማገዝ የደስታ ምንጫቸው መሆኑን ገልጸዋል። ዘጋቢ በቃሉ ክንዴ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 30
  • 👍 13
  • 🔥 1
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 27, 2026https://youtu.be/DzsmXiNH774?si=2asoRZmfS-VQt5em
  2. Sep 27, 2026ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የጭንቀት ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጭ…
  3. Sep 27, 2026photo post
  4. Sep 26, 2026የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ለሚገኘው ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በደሴና አካባቢው…
  5. Sep 26, 2026photo post
  6. Sep 26, 2026ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →