TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59779 5.31K
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የጭንቀት ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች፦

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም

ጭንቀት የተለመደ እና ሁልጊዜ የሚከሰት የሰው ልጆች የህይወት ክፍል ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታ በገጠማቸው ጊዜ ከሥጋት የተነሳ የሚሰማቸዉ ውጥረት፣ ጫና፣ ግፊትና የሐሳብ ወይም የስሜት አለመረጋጋት ሲሆን ሰዎች ለገጠማቸው እንግዳ ነገር/አስቸጋሪ ሁኔታ የተፈጠሮ ስሜታቸው የሚሰጠው ግብረ-መልስ /reaction/ ነዉ። ምንም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ የጭንቀት ስሜት አወንታዊ የሕይወት ገፅታ ባይሆንም ለሰው ልጆች እንደ መረጃ አቀባይ ሆኖ ያገለግላል።

ሰው በዕለታዊ ህይወቱ ውስጥ ውጥረት፣ ብስጭት፣ ንዴት፣ተስፋ መቁረጥ ወይም ቁጣ ሊፈጥሩ የሚችሉ አነስተኛ ጭንቀቶች በሕይወታችን ሊያጋጥሙን የሚችሉ  ቢሆንም  ጉዳት ላይ የሚጥሉን አይደሉም።

ሆኖም ግን ጭንቀቱ ከልክ ካለፈና የዕለት-ተዕለት ተግባረትን ማስተጓጐል፣ የስሜት ወይም የባሕሪ ለውጥና ሌሎች ምልክቶች መታየት ሲጃምሩ የጭንቀት ህመም ይሆናል። አንድሰው ለጭንቀት ህመም የመጋለጥ ሁኔታው የሚወስነው ግለሰቡ በህይወቱ የሚያገጥሙትን ችግሮች በአካላዊና በሥነ ልቦናዊ የመቋቋም ጥንካሬ ወይም ድክመትይወሰናል።

የጭንቀት ህመም ምልክቶች፡-
የድካም ስሜት፣ መጫጫን፣ ማዞር፣ ማቅለሽለሽ፣ የደምግፊት ከፍ ማለት፣ ለተወሰነ ጊዜ ቀዝቃዛ ላብ ፤ ያለምክንያት መቆጣት፣ የመሸበር ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ያለምክንያት መከፋትና ድብርት፣ በሀሳብ መሸነፍ፤ ቸልተኝነት፣ ግልፍተኝነት (ስሜትን አለማቆጣጠር)፣ የስሜት መዘበራረቅ፣ ጥፋተኝነትን ወደ ሌላ ለማሳበብ መፈለግ፤ በስራ ላይ ትኩረት ማጣት፣ ቀጠሮ መርሳት፤ ዉሳኔ መወሰን አለመቻል፤ የማሰብችሎታ መቀነስ፤ የአመጋገብ ልምዶችን መቀየር፣ ስለግል ንፅሕናው ግድየለሽ መሆን፣ ከሰዎች ጋር ብዙ መነጋገር አለመፈለግ፤ ዝምታን መምረጥ ወይም ከማህበራዊ ግንኙነቱ እራስን ማግለል ወዘተ….ናቸዉ

ጭንቀትን የምንከላከልባቸዉ መንገዶች፡-
• የጭንቀት መነሻ ምክንያቶችንና ችግሮችን መለየትና ማወቅ
• በተፈጠረዉ ችግር ምክንያት ደጋግሞ ራስን አለመዉቀስ
• ሌሎች ስለ እኔ መጥፎ ነገር ያስባሉ ብሎ አለመገመት
• እረፍት ማድረግና፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት
• አልኮል፣ ትምባሆ፣ ጫትና የመሳሰሉትን አለመጠቀም
• እራስን ማዝናናትና የአካል እንቅስቃሴ መስራት
• ከታማኝ ጓደኛ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር
• ተጫዋችና ቀልደኛ ለመሆን መሞከር ሁልጊዜ መሣቅ ያስፈልጋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 52
  • 👍 4
  • 🔥 4
  • 😁 1
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 27, 2026የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ህዝብ ለሠራዊቱ 15 ሰንጋዎችንና ሙክቶችን ድጋፍ አድርጓል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 17 ቀን 20…
  2. Sep 27, 2026photo post
  3. Sep 27, 2026https://youtu.be/DzsmXiNH774?si=2asoRZmfS-VQt5em
  4. Sep 27, 2026photo post
  5. Sep 26, 2026የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ለሚገኘው ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በደሴና አካባቢው…
  6. Sep 26, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →