በቀጠናው የሚገኘው ኮር ከሰሜን ወሎ ዞን አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም
ኮሩ ከሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ ከሚገኙ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በወቅታዊ የሠላም ሁኔታ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ደጀኔ ደበሌ በቀጠናው ተሰማርቶ የሚገኘው የኮሩ የሰራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሉና ከመስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት በፅንፈኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ሰላም በዘላቂነት የማረጋገጥ ተግባር የመፈፀም ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።
የፀረ ሰላም ሀይሎችን ፍላጎት ቀድሞ በመረዳትና የገቢ ምንጩን በማድረቅ ማንኛውንም ድጋፍ እንዳያገኝ በጋራ መስራት ይኖርብናል ያሉት ምክትል አዛዡ በህዝቡ ውስጥ ተደብቀው የፅንፈኞችን ፕሮፖጋንዳ የሚነዙና ዘረፍን የሚፈፅሙ ቡድኖችን ተከታትሎ በመያዝ እርምጃ በመውሰድ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል።
የወልድያ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደርበው አዳነ መከላከያ ሰራዊታችን ቀን ከሌሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ በቀጠናው ሲንቀሳቀስ በነበረው የፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰዱ አሁን ላይ በዞኑ ሰላም መስፈን ችሏል ለዚህም የዞኑ የፀጥታ አካላት ከሰራዊቱ ጋር በመሆን የሰሩት የሰላምና ፀጥታ ስራ ውጤት ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የፀጥታ አካላትም ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመቀናጀት ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመታገል የቀጠናውን ሰላም ለማረጋገጥ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ ጌትነት አስናቀው
ፎቶ ግራፍ ዮናስ ካንቻማ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Post #59741
5.05K
- ❤ 40
- 👍 12
- 🔥 1
- 🤯 1