አለም አቀፍ ህጎችን ያከበረ የግዳጅ አፈፃፀም ተመራጭና ለተሻለ ድል የሚያበቃ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019
ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከማዕከላዊ ዕዝ ሁሉም ክፍሎች ለተውጣጡ ኦፕሬሽናል እና የስታፍ አመራሮች ወታደራዊ ኢላማዎችን በመለየት የሲቪሊያንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ስልጠና መሠጠቱን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ አስተባባሪ ሚስተር ስኖዊ ሊንተን ገልፀዋል።
ከተጨባጭ ምልከታዎች በመነሳት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀገሪቱ የተስማማችባቸውን የጄኔቫ ስምምነቶች በማክበር ግዳጁን እየፈፀመ ነው። አሁን ላይ በሚከሰቱ ግጭቶች የተወሳሰቡ ስምሪቶችን በበሳል አመራር በመፍታት የሰላማዊ ዜጎች ከለላ ሊሆን ይገባል ሲሉ ሚስተር ስኖው አስገንዝበዋል።
በማዕከላዊ ዕዝ የህዳሴ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል እያሱ ሀፍቱ ተቋሙ የሚመራባቸው ህጎች ሰራዊቱ የሚገነባባቸው፤ ከህገ መንግስቱ የተወሰዱ እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝን የሚቃወሙ በመሆናቸው የድል አድራጊነቱ ሚስጢር ናቸው ብለዋል።
ስልጠናው በቀጥታ ወታደራዊ ስምሪትን ለሚመሩ አመራሮች መሰጠቱ በግጭት ቀጠና የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመለየት ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ ተቋማትን ከአላስፈላጊ አደጋ ለመታደግ ይረዳል ያሉት ከፍተኛ መኮንኑ ሰራዊቱ ዓለም አቀፍ የጦርነት ህጎችን እንዲረዳና በግዳጁ ላይ ግልፅ በመሆን በኃላፊነት ስሜት ተልዕኮዎቹን ማከናወን እንዲችል አቅም መሆኑን ተናግረዋል። የዘገበው መሀመድ አህመድ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Post #59737
4.79K
- ❤ 34
- 👍 7
- 🔥 1