TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59692 5.69K
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም

ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚያሥቀድመው ህወሃት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተጣምሮ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የግዳጅ ቀጣና በከፈተው ማጥቃት በዕዙ ሠራዊት ጠንካራ ክንድ የተመከተ ሲሆን ታጣቂዎቹን ጨምሮ የተለያዬ ዓይነት መሳሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል ህወሃት እና መሰል ተጣማሪ ቡድኖች በቀጣናው ሰብሮ በመግባት ህዝብን የመዝረፍ እና የመበተን ዓላማቸው መክሸፉን ገልፀው የዕዙ ሠራዊት በወሰደው ፈጣን የፀረ-ማጥቃት ምላሽ በህገ ወጡ ህወሃት ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን አሥረድተዋል።

ህወሃት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ አሸክመው ያጣመሩት ቡድኑ በሰሜን ወሎ ዞን ተኩለሽ ፣ ድልድይ ፣ቀይ አፈር ፣ በረሃ ማርያም ፣ ባይብዋ ፣በጭሮ እና ኩቤ ቀረንሳ በሚባሉ አካባቢዎች ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰልፎ ሾልኮ ለመግባት የሞከረ ሲሆን በደረሰበት ጠንካራ ምት ንብረት እና የሰው ኃይሉን እያንጠባጠበ ወደመጣበት ለመመለስ መገደዱን አዛዡ ተናግረዋል።

ሠላም ጠል የሆነው ቡድን በጀመረው እና ሠራዊታችን ባካሄደው መልሶ ማጥቃት በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችም ተማርከዋል።

በዚህም መሰረት 04 ዲሽቃ ፣ 22 መትረየስ ፣ 08 ስናይፐር፣ 50 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ ፣ 03 አርፒጂ7፣ 1ዐ አይኮም የመገናኛ ሬድዮ፣ 01 አይነት 77 የመገናኛ ሬድዮ፣ 03 የድሸቃ ወሳ እግር፣ 11 የአይኮም መገናኛ ባትሪ እና 12 አይኮም ቻርጀር ይገኙበታል። በተጨማሪም በርካታ የጠላት ኃይል ሲማረክ 272 ተገድሏል፣ 260 የጠላት ኃይል ቆስሏል።

አሁን ላይ ሠራዊቱ የጠላትን ሁኔታ እያነበበ ከያዛቸው ቁልፍ ወታደራዊ መሬቶች እየተወረወረ የተጠኑ ፀረ-ማጥቃቶችን በመፈፀም የግዳጅ ቀጣናውን ከጠላት የማፅዳት ወሳኝ ግዳጆችን በመፈፀም ላይ ይገኛል።

ዕድሜ ልኩን ከስህተቱ የማይማረው ህገ-ወጡ ህወሃት ካሰባሰባቸው ጀሌዎቹ ጋር ግንባር በመፍጠር የሞከረው የሽብር ተግባር በእንጭጩ እንዲቀጭ እና ዕዙ ድል እንዲቀዳጅ የአካባቢው ማህበረሰብ ላበረከተው ድጋፍና ሚና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ምስጋና አቅርበዋል። መረጃውን ያደረሠን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 57
  • 🫡 23
  • 👏 13
  • 👍 10
  • 🔥 5
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 26, 2026ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ…
  2. Sep 26, 2026photo post
  3. Sep 26, 2026ክፍለጦሩ 85 ሺህ ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የ6ኛ ዕዝ ፈንቅል…
  4. Sep 26, 2026photo post
  5. Sep 26, 2026የአካባቢው ህዝብና መስተዳደር በግዳጅ ቀጠና በመገኘት ሠራዊቱን አበረታቱ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የራያ ቆ…
  6. Sep 26, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →