TGViewer
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @fdredefenseforc · 42.7K subscribers
Post #59664 6.13K
ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፥ ለሀገሬ የምሰስተው ነገር የለም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፥ ለሀገሬ የምሰስተው ነገር የለም ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡

በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወትና የውትድርና ጉዞ ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡ 

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጀግኖችን ታሪክ በመፃፍ፤ ጀግኖችን በማወደስ ትውልድ ይገነባል፡፡

ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፤ እኔም ለሀገሬ የምሰስተው አንዳች ነገር የለም ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ መጽሃፉ ለዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም ለታሪክ ተመራማሪዎች የሚጠቅም መሆኑን አንስተዋል፡፡

ድል ቁርሱ መፅሃፍ ከኩየራ ወንዞች መሐል የፈለቀዉ የጦር ሊቅ በሚል ርዕስ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የህይወት  ታሪክ ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ነው።

ወታደራዊ ሁኔታን ከማንበብ እስከ ውጤታማ የድል ምዕራፍ ድረስ በማያቋርጥ የአመራር ሰንሰለት ዉስጥ ያለፉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሁሉም በላይ ሀገር እና ህዝብን ላስቀደመ ዓላማ ዕምቅ ወታደራዊ ሙያቸውን ያለ መታከት ያበረከቱበት እውነተኛ ታሪክ በመፅሃፉ ተካቷል።

በአማን ታደሰ ተፅፎ ለንባብ የበቃው መፅሃፉ ከጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ በጀግንነት የደመቀ ታሪክ ትውልድ እንዲማርበት በማድረግ በኩል የሚያበረክተው አሰተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመፅሃፉ ዙሪያ ምልከታቸውን የጋሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ሃያሲ ብርሃኑ ደቦጭ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በመፅሃፉ ላይ ያላቸዉን ምሁራዊ ዕይታ ለፕሮግራሙ አቅርበዋል

በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶክተር)፣ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በወንድማገኝ ታደሠ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • ❤ 51
  • 👍 16
  • 👏 10
  • 🔥 2
  • 😁 2
  • 🤔 1
  • 🏆 1
More from @fdredefenseforc
  1. Sep 25, 2026ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፀጥታ ኃይሎች ለተውጣጡ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 201…
  2. Sep 25, 2026photo post
  3. Sep 25, 2026ሠራዊቱ የአርሶ አደሮችን ሰብል የማረም ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በደቡብ ዕዝ ተወርዋሪው ኮከ…
  4. Sep 25, 2026photo post
  5. Sep 25, 2026በቀጠናው የሚገኘው ኮር ከሰሜን ወሎ ዞን አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019…
  6. Sep 25, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →