Post #46844
3.08K ለአንድ ወር ያህል ሲካሄድ የቆየው አገራዊ የምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ ፕላስ- ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ እየተከናወነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙርና በሃይማኖት አባቶች ጸሎት በተከፈተው በዚህ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የቀድሞ እና የአሁኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የአገር መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በጉባኤው ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡ 4 ሺህ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስምንት አጀንዳዎች ላይ ላለፉት ሳምንታት ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሀገራዊ_ምክክር #አዲስ_አበባ #NationalDialogue #ኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ኢትዮጵያ
Post #46843
4.87K Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Photo
ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርትና ተያያዥ አገልግሎቶች 474 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት፣ ከሀገር ውስጥ ዳታ ማይኒንግና ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሽያጭ 474 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለጋዜጣ ፕላስ እንዳስታወቁት፣ ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚሆነው በቀጥታ ለጎረቤት ሀገራት ከተደረገ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የተገኘ ነው። ቀሪው በሀገር ውስጥ ሆነው የውጭ ምንዛሬ ከሚከፍሉ የዳታ ማይኒንግና የቴክኖሎጂ ተቋማት የተሰበሰበ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስርን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዋና ተዋናይ ሆና እያገለገለች መሆኗን ያነሱት አቶ ሞገስ፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ጅቡቲና ኬንያ የሚደረገው የኃይል ኤክስፖርት በተሳካ ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ከኬንያ ጋር ያለው የኃይል ትስስር አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት እየታየበት እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
በሁለቱ ሀገራት ስምምነት መሠረት በከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ሰዓታት እስከ 200 ሜጋ ዋት እንዲሁም በዝቅተኛ የፍላጎት ሰዓታት ደግሞ 65 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እየቀረበ ይገኛል። የኃይል አቅርቦቱ የኬንያን የኤሌክትሪክ ሲስተም መረጋጋት ከማስጠበቅ ባሻገር፣ ሀገሪቱ ከውጭ ከምታስገባው ኢነርጂ እስከ 90 ከመቶ የሚሆነውን ከኢትዮጵያ እንድታገኝ አስችሏታል።
በሌላ በኩል፣ ወደ ሱዳን ይደረግ የነበረው የኃይል ኤክስፖርት ሀገሪቱ በገባችበት የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፤ በጦርነቱ ምክንያት በሱዳን በኩል ያለው የኢነርጂ ተሸካሚና አስተላላፊ መሠረተ ልማቶች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው የኃይል አቅርቦቱ ሊቆም ችሏል።
ከሱዳን ጋር የተፈጠረው የኃይል መቋረጥ ከመሠረተ ልማት ጋር ብቻ የተያያዘ እንጂ ከቀደመ ክፍያ ወይም ከውዝፍ ዕዳ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
የሀገር ውስጥ የኃይል ማመንጨት አቅምን በተመለከተ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከተያዘለት እቅድ ውስጥ 99 ነጥብ አምስት ከመቶ ያህሉን በማሳካት ከፍተኛ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። ሀገሪቱ ካመነጨችው አጠቃላይ 35 ቴራ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 51 ነጥብ አምስት ከመቶውን ወይም ከግማሽ በላይ የሚሆነው የተመረተው ከሕዳሴው ግድብ መሆኑንም አቶ ሞገስ ተናግረዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ባሻገር፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርኅ ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚና የሰላም ትስስር ለመፍጠር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
የአፍሪካ ኅብረት የ“አጀንዳ 2063” አካል የሆነውን የፋሲሊቲዎችና የመሠረተ ልማት ትስስር ግብ ለማሳካት ኢትዮጵያ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኗን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ ከኃይል ሽያጭ የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ በሀገር ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት አሁን ካለበት 54 ከመቶ ለማሳደግና አዳዲስ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
በዮርዳኖስ ፍቅሩ
Post #46841
2.39K በነገው ዕለት የተጠናቀረው የመጨረሻው ሰነድ ለአራት ሺህ ተሳታፊዎች ይቀርባል -ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- ዛሬ ምሽት 120ዎቹ አጠናቃሪዎች ከስምንቱም ቡድኖች የሚሰጡትን የመጨረሻ ግብዓቶች በማካተት የመጨረሻውን ሰነድ በነገው ዕለት ለ4ሺ ተሳታፊዎች እንደሚያቀርቡ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የምክክር ሂደቱ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ላይ መደረሱን የሚያሳይ መሆኑን ወይዘሮ ሒሩት አስታውቀዋል።
ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከስምንቱ ቡድኖች የተውጣጡ አጠናቃሪ ተሳታፊዎች ስራቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ የስምንቱንም ቡድን አጀንዳዎች አጠናቅሮ መሰነድ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስራ በመሆኑ የተወሰነ ጊዜ ወስዷል ብለዋል
በዚህም በትናትናው እለት የስምንቱም አጀንዳ ምክረ ሃሳቦች አንድ ወጥ የሆነ ሰነድ አዘጋጅተዋል። በዛሬው ዕለትም ለየስምንቱ ቡድኖች እየቀረበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ይህ ሂደትም እያንዳንዱ ቡድን ያለውን የመጨረሻ ግብዓት ማስገባት ያስችለዋል። ዛሬ ምሽት 120ዎቹ አጠናቃሪዎች የመጨረሻዎቹን ግብዓቶች በማካካተት የመጨረሻውን ሰነድ አጠናቅረው ያዘጋጃሉ ብለዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተዛቡ መረጃዎችን በመስማት እንዳይወዛገብ እና ትክክለኛ የሆኑ ሚዲያዎችን እንዲሁም የኮሚሽኑን ይፋዊ መግለጫዎች ብቻ እንዲከታተል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዳግማዊት አበበ
Post #46838
3.03K ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ│በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሀዊ ጉደና ወረዳ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ አራት የሶላር ሚኒ ግሪድ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በምርቃ መርሐግብሩ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) እነደገለጹት፤ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ያስገነቧቸው ናቸው።
የሶለር ሚኒ ግሪዶቹ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በሀዊ ጉዲና ወረዳ ባቴ፣ ቶርባን፣ ሃሮ ኦባና ሃሎ ጎባ ቀበሌዎች ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም አላቸው ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከ5 ሺህ 270 በላይ አባውራዎችንና የማህበራዊ ተቋማትን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም እንዳላቸው ያላቸው ሲሆን፤ አሁን ላይ በአራቱም ቀበሌዎች ከ840 በላይ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲችል የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታውበቀጣይም ከዋናው መስመር ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን በጸኃይ ኃይል ኢነርጂ ተደራሽ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
በሄለን ወንድምነው
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ጋዜጣ_ፕላስ #የፀሐይኃይልማመንጫ #ምዕራብሐረርጌ #ሶላርሚኒግሪድ #ኢትዮጵያ #GazettePlus #SolarEnergy #Ethiopia
Post #46836
2.72K “ትግራይ ወጣቶች በየቀኑ የሚታፈሱባት ፍትሕ አልባ ክልል ሆናለች” -ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ │ ትግራይ ወጣቶች የሚሰደዱባት፣ በየቀኑ የሚታፈሱባትና በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገቡባት ፍትሕ አልባ ክልል ሆናለች ሲሉ የስምረት ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ገለጹ፡፡
ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ የሕወሓት ቡድን በቅርቡ የትግራይን ሕዝብ መብት የሚጥስ አፋኝና ሕገ-ወጥ ሕግ አውጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ወጣቶች የሚሰደዱበት፣ በየቀኑ የሚታፈሱበትና ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገቡበት አሰጋጭና ፍትሕ አልባ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
በሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ምክንያት የትግራይ ሕዝብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛል ያሉት ፕሮፌሰር ክንደያ፤ ወጣቶች በተለያየ መንገድ ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ሌሎች ክልሎችና ወደ ጎረቤት ሀገራት በስደት በመውጣታቸው የክልሉ ከተሞች ወጣት አልባ እየሆኑ መጣታቸውን አስረድተዋል፡፡
ቡድኑ ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ እንደ መያዣ (ጋሻ) አድርጎ እየተጠቀመ መሆኑን በመጠቆም፤ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች በመጣሳቸው ምክንያት ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል አመርቂና አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት መሠረታዊ የሸቀጦች፣ የነዳጅና የሌሎች አቅርቦቶች እጥረት መከሰቱን የገለጹት ፕሮፌሰሩ፤ ይሁን እንጂ በፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ መሠረታዊ የስልክ፣ የትራንስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች ቀጣይነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ፣ ሕገ-ወጥ የሰውና የመሣሪያ ዝውውር በየከተማው እንደሚፈጸም አብራርተው፤ በአሁኑ ወቅት ክልሉ በከፍተኛ አጠቃላይ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
የሕወሓት ቡድን የጊዜያዊ አስተዳደሩን በማፍረስ በኃይል ሥልጣን መቆጣጠሩንና ክልሉን ጨምድዶ በመያዝ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ምርጫ ሲካሄድ በትግራይ እንዳይካሄድ ማድረጉንም አብራርተዋል።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ስምረትፓርቲ #ሕወሓት #ሰብዓዊመብት #ኢትዮጵያ #GazettePlus #Tigray #Ethiopia