በነገው ዕለት የተጠናቀረው የመጨረሻው ሰነድ ለአራት ሺህ ተሳታፊዎች ይቀርባል -ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- ዛሬ ምሽት 120ዎቹ አጠናቃሪዎች ከስምንቱም ቡድኖች የሚሰጡትን የመጨረሻ ግብዓቶች በማካተት የመጨረሻውን ሰነድ በነገው ዕለት ለ4ሺ ተሳታፊዎች እንደሚያቀርቡ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የምክክር ሂደቱ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ላይ መደረሱን የሚያሳይ መሆኑን ወይዘሮ ሒሩት አስታውቀዋል።
ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከስምንቱ ቡድኖች የተውጣጡ አጠናቃሪ ተሳታፊዎች ስራቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ የስምንቱንም ቡድን አጀንዳዎች አጠናቅሮ መሰነድ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስራ በመሆኑ የተወሰነ ጊዜ ወስዷል ብለዋል
በዚህም በትናትናው እለት የስምንቱም አጀንዳ ምክረ ሃሳቦች አንድ ወጥ የሆነ ሰነድ አዘጋጅተዋል። በዛሬው ዕለትም ለየስምንቱ ቡድኖች እየቀረበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ይህ ሂደትም እያንዳንዱ ቡድን ያለውን የመጨረሻ ግብዓት ማስገባት ያስችለዋል። ዛሬ ምሽት 120ዎቹ አጠናቃሪዎች የመጨረሻዎቹን ግብዓቶች በማካካተት የመጨረሻውን ሰነድ አጠናቅረው ያዘጋጃሉ ብለዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተዛቡ መረጃዎችን በመስማት እንዳይወዛገብ እና ትክክለኛ የሆኑ ሚዲያዎችን እንዲሁም የኮሚሽኑን ይፋዊ መግለጫዎች ብቻ እንዲከታተል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዳግማዊት አበበ
Post #46841
2.39K

- ❤ 2