የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል
+++++++++++++++++
በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ነው። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።
#Meskel #Demera #MeskelSquare #EthiopianHeritage #Ethiopia
Post #46911
1.36K





- ❤ 6
- 👍 1