ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
ውይይታችን በመከላከያና ደኅንነት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህልና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል።
በተጨማሪም ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
🇪🇹 🇷🇺
Post #46895
4.72K


- 👏 10
- ❤ 7
- 👍 3