TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46927 1.35K
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ
+++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በአንድ የታሪክ ገጽ ብቻ ተወስኖ ለመግለጽ መሞከር የሀገሪቱን ትልቅነት፣ የዘመናት ጥልቅ ጥበብና የሕዝቧን ሁለገብ ማንነት ካለመገንዘብ ይመነጫል።

ኢትዮጵያ ሺህ ዓመታትን በብዙ መልክ ያሳለፈች፤ ውጣ ውረዶችንም በትውልዶች ቅብብሎሽ የተሻገረች፤ የሥልጣኔ ከፍታዎችን የገለጠች፣ ነፃነቷን ጠብቃም የዛሬው ትውልድ እጅ የደረሰች ሀገር ናት። በውስጧም ብዙ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ እምነቶችና ማንነቶች በአንድ የሀገር ማንነት ውስጥ ተሳስረው የሚኖሩባት ናት።

ይህ መልከ ብዙ እና ጥልቅ ታሪክ ደግሞ መገለጫና መከሰቻውም ብዙ ነው። በአክሱም ግዙፍ ሐውልቶች፣ በላሊበላ የውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ በጎንደር ቤተ-መንግሥታት፣ በሐረር ጀጎል ግንብ፣ በጢያ ትክል ድንጋዮች እንዲሁም በኦሞና በአዋሽ ሸለቆዎች የሰው ልጅ ጥንታዊ ታሪክ ውስጥ ሆኖ ዛሬም በግልጽ ራሱን የሚገልጽ ሕያው ምስክር ነው።

በዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ (በሚዳሰስም በማያዳሰስም) የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶችም ይህን ታሪካዊ ጥልቀት ያረጋግጣሉ። ዩኔስኮ በኢትዮጵያ በርካታ ቅርሶችን የዓለም ቅርስ አድርጎ መመዝገቡም የዚህ አስረጂ ነው። ምክንያቱም ይህ የሚያሳየው፣ ሀገሪቱ ለዓለም ሥልጣኔ፣ ለሥነ-ሕንጻ፣ ለባሕልና ለሰው ልጅ ታሪክ ያላትን አበርክቶ ነው።

ነገር ግን ትናንት ታላቅ ነበርን ማለት፣ የዛሬን ታላቅነት ማረጋገጫ አይሆንም። ለምሳሌ፣ ቅርስ የሚከበረው በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን፤ ትርጉሙን ለአዲስ ትውልድ በማስተላለፍ....
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት_https://gw.press.et/am-digital-content/share/am-stories/4zwzpj4ph7hj2vq6pzm7xreqdd
More from @ethpress
  1. Sep 29, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።…
  2. Sep 29, 2026photo post
  3. Sep 29, 2026የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት +++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅ…
  4. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  5. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
  6. Sep 24, 2026‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →