የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት
+++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚተገበረው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት፣ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነትና የኢኮኖሚ አጋርነት የሚያጎለብትና ድንበር ተሻጋሪ የመሰረተ ልማት ውጥንን እውን አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ነዳጅ ለማጓጓዝ የሚወስደውን ጊዜ በመቀነስ የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናን የሚያፋጥን ነው። የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ አጋርነት ይተገበራል።
ከአንድ ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝና የማስተላለፍ አቅምም ይኖረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በተገኙበት ፕሮጀክቱ ይፋ ተደርጓል። ኢትዮጵያ የያዘችው ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እምቅ አቅሞችን ወደ ተግባር እየቀየረች ትገኛለች
የመሠረተ ልማት ትስስር እንዲሁም የኢነርጂ ዲፕሎማሲ በተለይም በታዳሽ ኃይል አቅርቦት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ለሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኬንያና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በተግባር እያጠናከረች ትገኛለች።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሀገር ውስጥ ብርሃን ከመሆን አልፎ ለቀጣናው ሀገራት የሚተርፍ ንጹህ የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማመንጨት የምሥራቅ አፍሪካን የኢንዱስትሪ መነቃቃት የሚያግዝ ትልቅ የልማት ሞተር ሆኗል።
#Ethiopia #CouncilOfMinisters #EthiopianGovernment #PolicyDecisions #AddisAbaba
Post #46916
755





