ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ│በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሀዊ ጉደና ወረዳ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ አራት የሶላር ሚኒ ግሪድ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በምርቃ መርሐግብሩ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) እነደገለጹት፤ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ያስገነቧቸው ናቸው።
የሶለር ሚኒ ግሪዶቹ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በሀዊ ጉዲና ወረዳ ባቴ፣ ቶርባን፣ ሃሮ ኦባና ሃሎ ጎባ ቀበሌዎች ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም አላቸው ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከ5 ሺህ 270 በላይ አባውራዎችንና የማህበራዊ ተቋማትን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም እንዳላቸው ያላቸው ሲሆን፤ አሁን ላይ በአራቱም ቀበሌዎች ከ840 በላይ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲችል የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታውበቀጣይም ከዋናው መስመር ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን በጸኃይ ኃይል ኢነርጂ ተደራሽ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
በሄለን ወንድምነው
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ጋዜጣ_ፕላስ #የፀሐይኃይልማመንጫ #ምዕራብሐረርጌ #ሶላርሚኒግሪድ #ኢትዮጵያ #GazettePlus #SolarEnergy #Ethiopia
Post #46838
3.03K


