የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማማ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰር የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በስምምነነቱ መሰረት ቦይንግ 777-8 እና ቦይንግ 777 ኤፍ የተባሉ አውሮፕላኖችን ይገዛል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አውሮፕላኖቹ ከ2033 እስከ 2035 ባለው ጊዜ እንረከባለን። በተለይም ሁለቱ በጣም ዘመናዊ ናቸው ብለዋል።
በተጨማሪም በ2027 እና 2028 ለርክክብ የሚደርሱ ሁለት ተጨማሪ የቦይንግ 777 የጭነት አውሮፕላኖች ግዢ እንደሚፈጸም ጠቅሰው፣ ከተሳፋሪ አውሮፕላንነት ወደ ጭነት የተቀየሩ 4 ተጨማሪ ቦይንግ 777 ካርጎ አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ ተናግረዋል።
የካርጎ አገልግሎቱ ከአጠቃላይ ገቢው ወደ 23 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን የጠቆሙት ተጨማሪ የጭነት አውሮፕላኖችን በመጨመር ዘርፉን ለማስፋፋት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቦይንግ የንግድ ሽያጭና ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 777-8 የካርጎ አውሮፕላን በማዘዝ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ በመሆኑ ዕውቅና እንሰጣለን ብለዋል።
ስምንት 777-8 የካርጎ አውሮፕላኖችን እና ሁለት 777 የካርጎ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ የአውሮፕላን ስብስቡን እያሳደገና የአገልግሎት አድማሱን በአፍሪካ እያሰፋ ይገኛል።
በዳግማዊት አበበ
Post #46931
875
