Post #46830
3.93K
Channel ✦ Verified Channel
GA Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
@ethpress
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
- Subscribers
- 24.8K
- Photos
- 41.3K
- Videos
- 346
- Links
- 5.8K
Showing posts older than #46832 · Back to latest
Older Posts 7 shown
Post #46828
3.14K

- ❤ 5
Post #46827
3.79K

የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን መወሰን ይጠበቅበታል - ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ሲል ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ተናገረ።
የሕወሓት አመራሮችና የትግራይን የወርቅ ማዕድን በኮንትሮባንድ መንገድ በመዝረፍ ላይ ናቸውም ብለዋል።የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን መወሰን ይጠበቅበታል።
ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት አስተያየት፤ የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ብለዋል።
የሕወሓት ቡድን የዓለም አቀፍ አሸባሪነትን መመዘኛዎች እያሟላ እንደሚገኝ ያነሱት ጋዜጠኛው፤ ቡድኑ ወጣቶችን ለሌላ ሀገር አሳልፎ በመሸጥ፣ ማዕድንን በመዝረፍና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ በመላክ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም ቡድኑ በትግራይ አካባቢ ያለውን የወርቅ ማዕድን በስፋት በመዝረፍና በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ ሌላ ሀገር በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይህንኑ የሀብት ዘረፋ እያካሄዱ የሚገኙት የፖለቲካ ኃይሎችና በተለይም የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ የበላይ አመራሮች መሆናቸውንም አስረድተዋል።
በክልሉ ባለው የሰላም እጦት ምክንያት ወጣቶች ወደ አዲስ አበባና ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በመሸሽ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ጋዜጠኛ ዳሞራ፤ በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ወጣቶች እስከ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ድረስ ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
መላው ኢትዮጵያውያን ክልሉ ከንቱ በሆኑ የራሱ ልጆች ሲጠፋ በዝምታ ማየት እንደሌለባቸውም ተናግረዋል።

- ❤ 7
- 👎 1
Post #46823
2.52K

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ጉዳዮች
✍️ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በታቀደውና በሚጠበቀው መሰረት ስራዎቹን በጥሩ ሁኔታ በማከናወን ላይ ይገኛል
✍️ በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙት 8 የምክክር ቡድኖች ውይይት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች በምክረ-ሀሳቦቻቸው ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ፊርማቸውን በማስፈር ስራቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው
✍️ በሂደቱ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ቢኖሩም ተሳታፊዎች በመወያየት ወደ አማካኝና የጋራ ሀሳብ መድረስ ችለዋል
✍️ ተሳታፊዎች በመደማመጥና በመወያየት ወደ አማካይና የጋራ ሀሳብ መድረስ የምክክሩን አስፈላጊነት አረጋግጧል
✍️ ከየስምንቱ ቡድኖች በተወጣጡ አባላት የተዋቀረ አዲስ ቡድን ተቋቁሟል፤
✍️ የቡድኑ ዋና ተግባር የምክረ-ሀሳቦቹን ወጥነት መጠበቅ፣ ድግግሞሾችን ማስቀረትና ሀሳቦች እንዳይቃረኑ ያደርጋል፣
✍️ በሂደቱ የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታ በተዘረጋው የቅሬታ መፍቻ ስርዓት መሰረት የመመርመርና ውሳኔ የመስጠት ስራ እየተከናወነ ነው
✍️ አጠቃላይ ስራው ሶስት አራተኛ ያህሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የምክክሩ ውጤት በቅርቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ይደረጋል
✍️ ለረጅም ጊዜ ሲደከምበት የቆየው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ውጤታማና ታሪካዊ ምዕራፍ ነው
#Ethiopia #NationalDialogue #PeaceBuilding #NationalConsensus #EthiopianPolitics

- ❤ 2
- 👍 1
- 👎 1
Post #46822
3.72K
Post #46812
3.31K

Post #46811
2.81K
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መርሐግብር ተካሂዷል።
ይህ ዝግጅት የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የኢኒሼቲቩን ተመራቂዎች እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድነት ያገናኘ ነው። ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን በመፍጠርም፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል።
መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።
በመቀጠል በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ልምዳቸውንና እይታቸውን ያካፈሉ አራት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ፓናሊስቶቹም፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሔም ደሴ፣ እንዲሁም የኢኒሼቲቩ ምሩቃን የሆኑት አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም ነበሩ።
ተሳታፊዎችና ወጣቶች ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣ በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉና በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች አበረታተዋል።
ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው። ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ አረጋግጧል።
#PMOEthiopia #DigitalEthiopia2030 #5MillionEthiopianCoders

- ❤ 1