የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ጉዳዮች
✍️ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በታቀደውና በሚጠበቀው መሰረት ስራዎቹን በጥሩ ሁኔታ በማከናወን ላይ ይገኛል
✍️ በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙት 8 የምክክር ቡድኖች ውይይት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች በምክረ-ሀሳቦቻቸው ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ፊርማቸውን በማስፈር ስራቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው
✍️ በሂደቱ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ቢኖሩም ተሳታፊዎች በመወያየት ወደ አማካኝና የጋራ ሀሳብ መድረስ ችለዋል
✍️ ተሳታፊዎች በመደማመጥና በመወያየት ወደ አማካይና የጋራ ሀሳብ መድረስ የምክክሩን አስፈላጊነት አረጋግጧል
✍️ ከየስምንቱ ቡድኖች በተወጣጡ አባላት የተዋቀረ አዲስ ቡድን ተቋቁሟል፤
✍️ የቡድኑ ዋና ተግባር የምክረ-ሀሳቦቹን ወጥነት መጠበቅ፣ ድግግሞሾችን ማስቀረትና ሀሳቦች እንዳይቃረኑ ያደርጋል፣
✍️ በሂደቱ የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታ በተዘረጋው የቅሬታ መፍቻ ስርዓት መሰረት የመመርመርና ውሳኔ የመስጠት ስራ እየተከናወነ ነው
✍️ አጠቃላይ ስራው ሶስት አራተኛ ያህሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የምክክሩ ውጤት በቅርቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ይደረጋል
✍️ ለረጅም ጊዜ ሲደከምበት የቆየው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ውጤታማና ታሪካዊ ምዕራፍ ነው
#Ethiopia #NationalDialogue #PeaceBuilding #NationalConsensus #EthiopianPolitics
Post #46823
2.52K




- ❤ 2
- 👍 1
- 👎 1