TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46827 3.79K
የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን መወሰን ይጠበቅበታል - ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ሲል ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ተናገረ።

የሕወሓት አመራሮችና የትግራይን የወርቅ ማዕድን በኮንትሮባንድ መንገድ በመዝረፍ ላይ ናቸውም ብለዋል።የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን መወሰን ይጠበቅበታል።

ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት አስተያየት፤ የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ቡድን ላይ ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ብለዋል።

የሕወሓት ቡድን የዓለም አቀፍ አሸባሪነትን መመዘኛዎች እያሟላ እንደሚገኝ ያነሱት ጋዜጠኛው፤ ቡድኑ ወጣቶችን ለሌላ ሀገር አሳልፎ በመሸጥ፣ ማዕድንን በመዝረፍና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ በመላክ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለይም ቡድኑ በትግራይ አካባቢ ያለውን የወርቅ ማዕድን በስፋት በመዝረፍና በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ ሌላ ሀገር በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ይህንኑ የሀብት ዘረፋ እያካሄዱ የሚገኙት የፖለቲካ ኃይሎችና በተለይም የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ የበላይ አመራሮች መሆናቸውንም አስረድተዋል።

በክልሉ ባለው የሰላም እጦት ምክንያት ወጣቶች ወደ አዲስ አበባና ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በመሸሽ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ጋዜጠኛ ዳሞራ፤ በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ወጣቶች እስከ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ድረስ ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

መላው ኢትዮጵያውያን ክልሉ ከንቱ በሆኑ የራሱ ልጆች ሲጠፋ በዝምታ ማየት እንደሌለባቸውም ተናግረዋል።
  • ❤ 7
  • 👎 1
More from @ethpress
  1. Sep 29, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።…
  2. Sep 29, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በ…
  3. Sep 29, 2026photo post
  4. Sep 29, 2026የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት +++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅ…
  5. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  6. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →