TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46811 2.81K
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መርሐግብር ተካሂዷል።

‎ይህ ዝግጅት የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የኢኒሼቲቩን ተመራቂዎች እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድነት ያገናኘ ነው። ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን በመፍጠርም፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል።
‎
‎መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።
‎
‎በመቀጠል በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ልምዳቸውንና እይታቸውን ያካፈሉ አራት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ፓናሊስቶቹም፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሔም ደሴ፣ እንዲሁም የኢኒሼቲቩ ምሩቃን የሆኑት አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም ነበሩ።

ተሳታፊዎችና ወጣቶች ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣ በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉና በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች አበረታተዋል።

ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው። ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ አረጋግጧል።

#PMOEthiopia #DigitalEthiopia2030 #5MillionEthiopianCoders
  • ❤ 1
More from @ethpress
  1. Sep 29, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።…
  2. Sep 29, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በ…
  3. Sep 29, 2026photo post
  4. Sep 29, 2026የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት +++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅ…
  5. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  6. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →