Post #7274
556 Oct 7, 2026, 17:40 UTC ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለቃችሁ ውጡ !!! የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ። የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ተደርጎ ተወስዷል። ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። #Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ትግራይ #ጦርነት #ኤርትራ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7271
542 Oct 7, 2026, 15:30 UTC የደብረጽዮን ጠባቂዎች በድሮን ጥቃት ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመቐለ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ በዓድዋ ከተማ በሚገኘው ሶሎዳ ሆቴል"ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ዒላማ ያደረገ ነበር። በጥቃቱ ወቅት የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፣ የእርሳቸው ጠባቂዎች ግን በዚሁ የድሮን ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። በጥቃቱ በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የታጠቁ የጥበቃ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ቀሪዎቹ ሦስቱ በወቅቱ በሆቴሉ ያረፉ/ሲስተናገዱ የነበሩ ሲቪሎች ሲሆኑ፣ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ዶ/ር ደብረጽዮንን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ከፍተኛ ኃላፊዎች በሆቴሉ ስለመኖራቸው እስካሁን የወጣ ይፋዊ መረጃ የለም። የመከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በዓድዋ ከተማ ሆቴሎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ከ4 ጊዜ በላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ይህም እርምጃ አመራሮቹ ያሉባቸውን አቅጣጫዎች ዒላማ ካደረገ የአየር ላይ ክትትል ጋር ተያይዞ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል። #Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ትግራይ #ጦርነት #ግብፅ #ኤርትራ #ሶማሊያ #ሱዳን #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7266
770 Oct 7, 2026, 10:23 UTC ምክርቤቱ ሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ቀየረ። እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች፦ 👉 ቀድሞ "የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር" በሚል 👉ቀድሞ "የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል። በተጨማሪም 👉 ቀድሞ "የፕላንና ልማት ሚኒስቴር" የነበረው "የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር" በሚል 👉ቀድሞ "የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" የነበረው "የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" በሚል ስያሜያቸው መቀየሩ ተገልጿል። #Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ምክርቤት #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7259
815 Oct 6, 2026, 17:10 UTC ኢሕአፓ በእስር ላይ የሚገኙት አባላቱ የዋስትና ውሳኔ ይፈጸም ወይም ይግባኙ በአፋጣኝ ይታይ ሲል ጠየቀ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) በእስር ላይ ያሉ የፓርቲው አባላት በተመለከተ ቀደም ሲል የተሰጠው የዋስትና ውሳኔ እንዲፈጸም ወይም በውሳኔው ላይ የቀረበው ይግባኝ በአፋጣኝ ተመርምሮ ተገቢው የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ይስሐቅ ወልዳይ፣ አባሉ አበበ ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተጠሪው ደረጄ ደለና እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉስ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከተደጋጋሚ የምርመራ ቀጠሮዎች በኋላ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበር አስታው፤ የፌዴራል ፖሊስ በዋስትና ውሳኔው ላይ ይግባኝ በማቅረቡ ጉዳዩ በይግባኝ ሂደት ላይ ይገኛል፤ በዚህም ተጠርጣሪዎቹ እስካሁን ከእስር እንዳልተለቀቁ አመልክቷል። ኢሕአፓ የዋስትና ጉዳዩ በአፋጣኝ እንዲታይ፣ ቀደም ሲል የተሰጠው የዋስትና ውሳኔ እንዲፈጸም ወይም ይግባኙ በፍጥነት ተመርምሮ ተገቢው የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። በተጨማሪም የተጠርጣሪዎቹ የግል ነፃነትና የፍትሕ መብት እንዲከበር፣ የፍርድ ሂደቱም በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች እንዳይጓተት እና የፍርድ ቤቶች ነፃነትና ገለልተኛነት እንዲጠበቅ አሳስቧል። ፓርቲው የአባላቱ ጉዳይ በፍጥነት፣ በግልጽነትና በሕግ መሠረት እንዲታይ በመግለጫው አሳስቧል። #Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አዲስ_አበባ #ኢህአፓ #ትብብር #የፖለቲካ_እስረኞች #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7257
813 Oct 6, 2026, 17:10 UTC የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ ሰላም ኃይል (APF) አደረጃጀት ተደራጁ። የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ቀያቸው የተመለሱ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎችንና ፈቃደኛ ግለሰቦችን «የአማራ የሰላም ኃይል» በሚል ስያሜ አደራጅቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያሰማራ መሆኑን ተሰምቷል። ታጣቂዎቹ አካባቢያቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ የተደራጁ ሲሆን፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ዲሲፕሊን እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል። የጎንደር አካባቢ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሰማሩ ሲሆን፣ በወሎም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ ይገኛሉ። ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ከፒቴን ማስረሻ ሠጤ አዲሱን አደረጃጀት በማዋቀር ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ተገልጿል። አደረጃጀቱ በትግራይ ክልል ከተቋቋመው የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ተሞክሮ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ የአካባቢውን ሁኔታና የመስኩን አካሄድ በጥሩ ሁኔታ የሚያውቁ አባላትን በመጠቀም ሌሎችንም ወደ ሰላም አማራጭ የመመለስና አካባቢውን የማረጋጋት ዓላማ ያለው ነው ተብሏል። #Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ፋኖ #ትብብር_ለህልውና #የአማራ_ሰላም_ሀይል #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና