የደብረጽዮን ጠባቂዎች በድሮን ጥቃት ሕይወት ማለፉ ተገለጸ።
የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመቐለ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ በዓድዋ ከተማ በሚገኘው ሶሎዳ ሆቴል"ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል።
አሁን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ዒላማ ያደረገ ነበር።
በጥቃቱ ወቅት የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፣ የእርሳቸው ጠባቂዎች ግን በዚሁ የድሮን ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
በጥቃቱ በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የታጠቁ የጥበቃ አባላት መሆናቸው ታውቋል።
ቀሪዎቹ ሦስቱ በወቅቱ በሆቴሉ ያረፉ/ሲስተናገዱ የነበሩ ሲቪሎች ሲሆኑ፣ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ዶ/ር ደብረጽዮንን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ከፍተኛ ኃላፊዎች በሆቴሉ ስለመኖራቸው እስካሁን የወጣ ይፋዊ መረጃ የለም።
የመከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በዓድዋ ከተማ ሆቴሎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ከ4 ጊዜ በላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ይህም እርምጃ አመራሮቹ ያሉባቸውን አቅጣጫዎች ዒላማ ካደረገ የአየር ላይ ክትትል ጋር ተያይዞ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።
#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ትግራይ #ጦርነት #ግብፅ #ኤርትራ #ሶማሊያ #ሱዳን #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7271
525

- ❤ 4