የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ ሰላም ኃይል (APF) አደረጃጀት ተደራጁ።
የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ቀያቸው የተመለሱ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎችንና ፈቃደኛ ግለሰቦችን «የአማራ የሰላም ኃይል» በሚል ስያሜ አደራጅቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያሰማራ መሆኑን ተሰምቷል።
ታጣቂዎቹ አካባቢያቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ የተደራጁ ሲሆን፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ዲሲፕሊን እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል።
የጎንደር አካባቢ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሰማሩ ሲሆን፣ በወሎም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።
ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ከፒቴን ማስረሻ ሠጤ አዲሱን አደረጃጀት በማዋቀር ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ተገልጿል።
አደረጃጀቱ በትግራይ ክልል ከተቋቋመው የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ተሞክሮ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ የአካባቢውን ሁኔታና የመስኩን አካሄድ በጥሩ ሁኔታ የሚያውቁ አባላትን በመጠቀም ሌሎችንም ወደ ሰላም አማራጭ የመመለስና አካባቢውን የማረጋጋት ዓላማ ያለው ነው ተብሏል።
#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አብይ_አህመድ #ፋኖ #ትብብር_ለህልውና #የአማራ_ሰላም_ሀይል #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7257
885


- 👎 8
- ❤ 2
- 🥰 1