TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #2328 · Back to latest

Older Posts 14 shown
Post #2327 801
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


2004-2014 ድፍን አስር አመት በጟደኝነት


እሱ #ሙስሊም እኔ #ኦርቶዶክስ እሱ #የአርሰናል ደጋፊ እኔ #የማንችስተር_ዩናይትድ እሱ #ዝምተኛ እኔ #ቀውጢ እኔ #አሸናፊ ከሆንኩ በጣም አበሳጪ እሱ ደግሞ ለኔ #ስሜት የሚጨነቅ ብዙ ቅጣቶችን የሚያልፈኝ........ከአፋ ብዙ መጥፎ ነገርች የማይወጡት እኔ ደግሞ ሰው ከተናገረው አይደለም የተናገረው ከመሰልኝ አካኪ ዘራፍ የምል.....


ትውውቃችን ትምህርት ቤት ውስጥ ነው ኳስ ስንጫወት ተቃራኒ ሆነን ነው እሱ ተከላካይ እኔ አጥቂ ሁሌም ተቃራኒ ሆነን ነው ምንገባው ፍልሚያው የሌለ ይጦፋል እሱም አደገኛ ተከላካይ ነው እኔም ለማግባት ተደጋጋሚ ወደ ጎላቸው እደርሳለሁ ሁሌ እኔ ላይ ነው ፋዎል የሚሰራው እንደደመኛ ነው ምንተያየው........እንደዛ እያልን ጟደኛሞች ሆንን ሰው ጟደኛ ሲሆን ይተዛዘናል የኔና የሱ ግን ባሰ ጌም ውስጥ የምንሆነውን አይቶ ማንም መልሰው ያወራሉ አብረው ይሔዳሉ የሚል አልነበረም እኔ እና እሱ ግን ከጌም በኃላ እየተበሻሸቅን ምግብ ልንበላ አብረን እንሔዳለን ተሻምተን እንበላለን...........

በተለይ ደግሞ የማይቀረው #ዶናት ነው እየተመንታተፍን ነው የምንበላው..........

ማሜ የኔ ምርጥ ወንድም....🥰😍🥰


እኔ 7A..........እሱ 7B ክፍል ነበርን በትምህርትም እንፎካከራለን እኔ እዘርረዋለሁ እንጂ ሃሃሃሃሃሃ ውጤት ስንቀበል ሁሌ እንዳበሸኩት ነበር በጣም ነበር የምናጠናው ከትላንት የተሻለ ለመሆን ነበር ጥረታችን ለጨዋታ የምንሰጠው ጊዜ አለን ለትምህርታችን ደግሞ ትልቁን ጊዜ....ለዛም ነው ውጤታችን አመርቂ የነበረው እንደውም እንዳንዶች ይገርማቸው ነበር ክላስ ላይ ጠንካራ ስንሆን...
ትልቅ ህልም ነበረን....ልናሳካው የምንመኘው


ውይ እረስቼ ፕሌስቴሽን አልችለውም ነበር እንባዬን ነው የሚያመጣው ውውውው 3:0 4:0 ምናምን ነው የሚያሸንፈኝ የነበረው 😡😡😡


ቤተሰቦቻችን ይተዋወቃሉ እኛጋር ለበዓል ለማሜ ተብሎ ለብቻ ነው ምግብ የሚሰራለት በተለይ ለመስቀል በዓል ለዛ ለልጄ ላዘጋጅ ትላለች እናቴ😂😂 ለዛ ልጄ ብላ ለኛ የተሰራው ሁሉም ሳይቀር ለሱ ትሰራለች ሁሉንም ታስቀምጣለች ይኽው አንድ በዓል ሳይቀር ድፍን አስር እመት.........



ብጣም የምወደው ወንድሜ አድማጬ ወደመጥፎ ስሔድ በምክሩ የሚመልሰኝ መልካሙን የሚመኝልኝ ለህልሜ መሳካት ደፋ ቀና የሚልልኝ የኔ የሆኑትን የሚወድ ተቀናቃኜ አጥቼ ሊያየኝ የማይፈልግ እኔ የኔን አስቸጋሪ ፀባይ ችሎ እንደዚ መሆን አለበት እንዲ ቢሆን እንዲህ ነው እያለ እየመከረ ሲጨንቀኝ ተጨንቆ እኔን እያለ ክሩቅ እየመጣ ብቻ ስንቱን ስላንተ ማውራት ጉንጭ ማልፋት ነው.....::

ወንድሜ የኔ ሰው #መሐመድ_ዑመር


እንኳን ደስ አለህ እንኳን ለዚች ቀን አደረሰህ አንተ ከዚህም በላይ ነው የሚገባህ ያኔ ልጆች ሆነን ያለምነውን አሳክተነዋል ሁሌም እልህ የለ ጥሩ ሰዎች መልካም ነገር ይገባቸዋል ፈጣሪ ከነሱ ጋር ስለሆነ ያሰቡትን ያሳኩታል እልህ አልነበር እንኳን ደስ አለህ #ማሻ_አላህ


😍🥰🥰🥰😍😍🙏🙏🙏💪🏿💪🏿💪🏿😘😘
Post #2319 654
አንተ ሁሉን ስለምታውቅ እንጂ ማን ሰላማችንን ይሰጠን ነበር::

አንተ ነህ በሰው ሁሉ ልብ ያለውን ምትመረምረው አንተ ብቻ ነህ እኔነቴን የምትረዳ ማን እንደሆንኩ የምታውቅ.......

አንተ ብቻ አምላክ አንተ ብቻ ጌታ..........

@jahABP


🥺🥺🥺🥺🥺🥺🙏🙏🙏🙏🙏😰😰😰
Post #2318 711
AB PHOTOGRAPHY

በነገራችን ላይ በቀን ከቀን ስራዎቼ አንዱ ጟደኞቼ ብጊዜ ወደቤት እንዲገቡ ማስታወስ ነው........እነሱም ሁሌ ይረሱታል እኔም ሁሌ አስታውሳለሁ ....እኔም አይሰለቸኝም እነሱም ጭቅጭቄ አይሰለቻቸውም አንድ ቀን ለውጥ ይመጣል ብዬ ተስፋ ሳልቆርጥ አለሁ.........


እኔ ብረሳ እንኳ ሰእራሳቸው ደውለው አብዬ እየገባሁ ነው አሰለቸሁሽ አ ይኽው በር ጋር ደርሻለሁ ነገ እመጣልሻለሁ ይሉኛል......ተወዳጆቹ


እባክህ ልጄ አንተጋር ከሆኑ ላክልኝ የምትለው የብዙ እናቶች ድምፅ ሁሌም ጭንቅላቴ ላይ ይቃጭልብኛል......እና ስለነሱ አብዝቼ አስባለሁ.......


እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃችሁ የሁላችሁንም የእናታችሁን ፀሎት ይስማና ይለውጥልን😍🙏🙏🙏

@jahABP ነኝ መልካም ምሽት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2316 654
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🥲🥲🥲🥲🥲🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥲🤦‍♂️🤦‍♂️🤦‍♂️🤦‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️
Post #2315 642
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ዛሬም_መበደል

ቀራኒዮን ስንመለከት በዓለም ላይ ክፉ የሆኑ ሁለት ሽፍቶችና የመጨረሻደግ ክርስቶስን እናገኛለን፡፡

ይቺ ምድር እነዚህን ወገኖች በፍርድ አስወግዳለች፡፡ እጅግ ደግና እጅግ ክፉ ለሆኑት ቦታ የላትም ፡፡ በዚህ አለም ላይ ስፍራ ያላቸው መካከለኞቹ ወይም ተጣጣፊዎቹ ናቸው፡፡ በጌታችን ቀኘና ግራ የተሰቀሉት ወንበዴዎች ጌታን ይሰድቡት ነበር፡፡

#ቅጣት_ሰውን_የተሻለ_አያደርገውም፡፡
እነዚህ ሰዎች ወደ ሞት እየሔዱ እንኳን ገና ይበድላሉ፡፡
ከሁለቱ ወንበዴዎች የቀኙ ወንበዴ( ፌያታዊ ዘየማን) በኀላ ተመልሷል፡፡ የተመለሰው ተዓምራት አይቶ አይደለም፡፡ ተዓምራት የተከናወነው ቆይቶ ነው፡፡

እርሱ ግን ያመነው ገዳዮች ባላሸነፉት በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡
ጌታችን:- "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ባለው ጊዜ ወንበዴው ተረታ ፡፡ የጌታ ፍቅር እንደአለት የጠነከረውን የወንበዴውን ልብ አቀለጠው፡፡ ገዳዮቹን ይቅር ያለ እኔንም ይቀበለኛል ብሎ አመነ፡፡

ተዓምራት ያዩ የጌታ ተከታይ መሆን አይችሉም ሰይጣን የበለጠ ተዓምራት ሲያሳያቸው እርሱን ይከተላሉ፡፡ ፍቅር ግን በእግዚአብሔር ቤት ይተክላል፡፡

በስተግራ በኩል የተሰቀለው ወንበዴ ግን እስከ መጨረሻው ልቡ ፀና፡፡ ጌታንም መውደድ አቃተው፡፡ በዚህም ምክንያት ከሕይወት ራሱን አገለለ፡፡ ሁለቱ ወንበዴዎች በዘመናት ሁሉ በአንድ ሀሳብ ተስማምተዋል፡፡ #እንግደል በሚል በሚል እቅድ እንኳን ተጣልተው አያውቁም፡፡ አሁን ግን በክርስቶስ ተለያዩ፡፡ በአንድ መንገድ የመጡ ቀራኒዮ ላይ ሲደርሱ በመንታ መንገድ ይሔዳለሁ፡፡

#ክርስቶስ_ልዩነት_ነው፡፡

ወንጀለኘነታችንን የወደዱልን አሁን ግን ታሪክ ለዋጩን ጌታ መውደድ ያቅታቸዋል፡፡
በቀኙ ወንበዴና በግራው ወንበዴ መካከል ያለው ልዩነት ኃጢያተኛ አለመሆን አይደለም፡፡ ምህረት ማግኘትና አለማግኘት ነው፡፡ በእኛ እና በዓለም ባሉት መካከል ያለው ልዩነትም ኃጢያተኛ አለመሆን አይደለም፡፡
እኛ #ምህረት_ያገኘን_ሀጢያተኞች_በመሆናችን_ብቻ_ነው፡፡

በግራ በኩል የተሰቀለው ወንበዴ:- "አንተ ክርስቶስ አይደለህምን?? እራስህንም እኛንም አድን" ብሎ ሰደበው፡፡ የክርስቶስን ጌትነቱን ካደ፡፡ የቀኙ ግን:- "ጌታ ሆይ" አለው ፍርድ የተዛባበትን ጌታሆይ ማለት እርቃኑን አብሮት ከተሰቀለው መንግስትን መለመን ትልቅ እምነትን ይጠይቃል፡፡ የቀኙ ወንበዴ በህይወት ዘመኑ ዛሬ ጓደኛውን ተቃወመው ፍቅርና ፍርድ በማይበግረው ማንነት ተደነቀ፡፡ ከዚህ በኀላ የቀረው የሰዓታት ዕድሜ ነው፡፡ እስከመጨረሻው ለግፍ ታማኘ በመሆኑ አሳዘነው፡፡

ሁሉም ነገር ገደብ ያስፈለገዋል፡፡
ሽፍታነትም ደንዳናነትም ክፋትም ምቀኘነትም ልክ ያስፈልገዋል፡፡ ያ ወንበዴ ግን ሀጢያትን ያለ ጡረታ እያገለገለ ነው፡፡

በእውነት ዛሬ ወደ ሞት እየሔዱ ቤተሰቦቻቸው በስንት ጭንቅ ውስጥ እያለፈ አሁንም እግዚአብሔርን የማይፈሩ አሁንም ለክፋታቸው ልክ ያጡ ስንቶች ይሆኑ?? አጠገባችኝ ስንቱ በሞት እየተንሸራተተ ስንቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ዘመኑ እየተቀጨ አሁንም ጌታን የማንፈራ ስንቶች ነን?? እነዚያ በሞኘነት የሞቱ እኛ ግን በብልጠት የቀረን የሚመስለን አያሌ ነን፡፡

ጌታ ሆይ እባክህ እንደቀኙ ወንበዴ በቀረን ዘመን አንተን ማመንና መታዘዝ ይሁንልን፡፡
አለም ለምኔ በሚያሰኘው ዘመን ገና ጭቃ እያላቆጥን ነውና እባክህን ይቅር በለን፡፡

ቅጣት የተሻለ ሰው አያደደርገንም፡፡በፍቅርህ መልሰን፡፡

የመፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡

@jahABP ነኘ ዛሬም ከመበደል እርሱ በቸርነቱ ይጠብቀን፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁ፡፡😍😊😊🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2310 726
ከትላንት ወዲያ ዳግማዊት ክፍሌን(ዳጊ ሾው) instagram ላይ live አውርቻት ነበር::

ከዛ ነትላንት አቤል ሲኒማ በተዘጋጀው የዳዊት ድሪምስ የማነቃቂያ ዝግጅት ላይ እሷ ተጋባዥ እንደሆነችና እዛ ብመጣ እንደምንገናኝ ነግራኝ እንደምመጣና ስጦታም እንድምሰጣት ነግሪያት በደስታ ተቀብላ እዛው እንገናኝ ተባብለን ተሰነባበትን::




እናም በቃሌ መሰረት ቦታው ድረስ ሔጄ የዳጊን አስገራሚ ታሪክ ሰምቼ ብዙ ነገር ተምሬ ስጦታዬን ሰጥቻለሁ በጣም ደስ ብሏት ነበር በጣም አሪፍ ጊዜ ነበር::

ይሔን ፎቶ ያነሳሁት ላንጋኖ ነው እዛ የሔዳችሁ ይህን ዘንባባ ላለመውደቅ ከማዕበሉ ጋር ምን ያህል ትንቅንቅ እንደሚያደርግ ሳታስተውሉ አትቀሩም እናም እንደ ዳጊ አይነት ደግሞ የህይወት ማዕበል በብርቱ ሲፈትናቸው ሳይወድቁ እዚ ደርሰዋል እናም ይህ ፎቶ እንደዳጊ አይነት ሴት እህቶቻችንን ይገልፃል ብዬ አሰብኩና ስጦታ ልሰጥ ወድድኩ::


ሴት ልጅ እንደዚ ጠንካራ ሆና ማየት ምንኛ ደስ ይላል.🥰🙏😍 ትልቅ ፍቅርና አክብሮት ዳጊ🙏🥰😍


እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ደግሞ አንድ ቀን እንግዳሽ እንደምታደርጊኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ::
Post #2303 765
በጣም እወዳቸዋለሁ ምትላቸውን ሰዎች ለምንድነው የምትወዳቸው????????


ጥንቃቄ አንድ

ማንም ይሁን ማን መጥፎ ነገር ስታደርጉ እናንተን ደግፎ የሚቆም ሰው ካለ እሱ እራሱ ልትፈሩት ልትጠነቀቁት የሚገባ ሰው ነው...ምክንያቱም የናንተን መጥፋት መንገድ ጠራጊ ነውና........

እኔ ምን አገባኝ ግን አስቡበት ለራሳችሁ ብዬ ነው::

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ::
Post #2300 690
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አብያ ወዴት ልትሔድ ነው አለኝ.......?

ከተኛሁበት ተነስቼ ልብስ ብቻ ቀይሬ ቁጭ ብያለሁ በደንብ አልነቃሁም ጥሩ እንቅልፍ አላገኝሁም ቁንጫዎቹ ምንም ሊያስተኙኝ አልቻልኩም በሉኝ አይገልፀውም ሰውነቴ ትንሽ ነገር ነው የሚበቃው ቀላልቷል አብጧል በግድ ነው የነጋልኝ ኦህህህህ:: ለነገሩ ገዳም ተኪዶ ጥሩ ፍራሽና አልጋ አይጠበቅ የታወቀ ነው::

አይ የትም ማታ ቁንጫዎቹ አላስተኛ ብለውኝ ምንም እንቅልፍ አልጠገብኩም ልብስ ቀይሬ ዞር ዞር ልበል ብዬ ነው አልኩት........

የት እዛው ቦታክ ልቴድ ከሆነ እነ አባ ፅዱ ስር ስብሰባ ንገር ይዘዋል አለኝ::

ውውውው ሲያበሳጭ በናትህ እና የት ልሆን ነው......
በቃ ተራራዋ ላይ ውጣ አለኝ እንደውም የጠዋቷን ፀሀይ ትሞቃታለህ......


ከገዳሟ ፊትለፊት ሶስት የተያያዙ ትንሽዬ ተራሮች አሉ እላዩ ብቻ ነው ሳር ከስሩ ሙሉ ቡሙሉ ድንጋይ ነው ሁሌም ሳየው ይገርመኛል ከስር ቆሜ ወድላይ ሳይ ከትልቅዬ ድንጋይ ጋር እጋጫለሁ ከላዩ ሳር ያለውም አይመስልም::


አንድ ጊዜ በጣም ስገረም ያዩኝ አባት እንዲህ ሲሉ ታሪኩን አጫወቱኝ.......


ይገርምኻል ይህ የምታየው ተራራ በሶስቱ ስላሴ ስም ነው የሚጠራው....

እውነት??? አልኩኝ ደሞ ሶስቱም ልከኛ ናቸው

እንዲቀጥሉልኝ መገረሜን አሳብቄ እውነት ነው አባታችን??? አልኩኝ.........

አዎ በጣም ሚስጥራዊ ቦታ ነው ይህ የምታየው ድንጋይ በሚስጥራዊ ኮድ ይከፈታል አሉኝ.........

ምን አልኩኝ በጣም ተገርሜና ተደንቄ......??? (እንዴት ሆኖ በትልቅ ስካቫተርም ሚከሰከስ የማይመስለውን የድንጋይ ግድግዳ በኮድ ነው የሚከፈተው ሲሉኝ ምን ልበል....)

አዎ ልጄ ብለው......ደሞ የዚ ኮድ ከፋች.................................ብለው ትልቁን ጥልቁን ታሩክ አጫውተውኛል.........ይቺ ሚስጥረኛ ሀገር................

እውነትህን ነው እዛው ልውጣን ልቀመጥ አልኩት

በቃ በኃላ ሲመችህ አንድ መፅሐፍ ታቀብለኛለህ አለኝ

ምንም ችግር የለም ወንድሜ እሺ አልኩት........ይቀጥላል............ወይም አይቀጥልም ብቻ ጠብቁኝ..............


ይሔን ታሪኬን አጫውቼሃለሁ ግን አብዬ ትለኛለች.............??

የቱን???

ብዙ ጊዜ ታሪኳን መሳጭ የህይወቷን አጋጣሚዋን ስላጫወተችኝ የነገረችኝ እንዳይሆን ብዬ


የእማን የውሃውን ታሪክ.... ባለፈው እኮ አንድ ጥግ ላይ እናቴ ቆማለች ሰዎችን ውሃ እየቀዱ ነው እናቴ በደስታ ፊት ሆና ነው የቆመችው አላየችኝም ቆሜ እያየኃት ነው በፊት ውሃ ለመቅዳት የምናየው ፍዳ እና ስቃይ ፊቴ ላይ ውልብ አለብኝ ውይ የኔ ምስኪን እናት በስንቱ ስቃይሽን በላሽ......ግን የፈጣሪ ስራ ይገርማል ያሁሉ አልፎ አሁን እናቴ አሁን ከአንድም ሁለት ቧንቧ አላት......አንተ መጥፎ አትስራ እንጂ ፈጣሪ ለሁሉም ነገር መልስ አለው...... ለዚህ እኛ ምስክሮች ነን እናቴ ቅን ሰው ነች ቅን ሰዎች ሚገጥሙት ፈተና ሁሉ ገጥሟታል.....


አንዴ ምን ሆነ መሰለህ...............



አብይ የማርያም ልጅ ነኝ ጠብቁኝ እንደበፊቱ እመጣለሁ

🦶🏿🦶🏿🦶🏿👣👣👣👣👣



@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →